አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ታማኝ በየነና ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ።
ፖለቲከኛ ነአምን ዘለቀ እና ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳም ወደ ግንባር ከዘመቱት መካከል ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የህልውና ዘመቻ በተለያየ መንገድ ከፊት ሆነው ሲታገሉ የነበሩ አርቲስቶች እና የቀድሞ ሠራዊት የጦር አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመትን ተከትሎ እነሱም እንደሚዘምቱ ከዚህ ቀደም ቃል ገብተው ነበር።
በዚህም መሠረት በዛሬው እለት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ወደ ግንባር ዘምተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!