Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል እየሰበሰቡ ነው፡፡
ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች የሚሰበሰቡበት በመሆኑ የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል የመሰብሰብ ተግባር ከህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ይኸው ተግባር በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ኮሌጆች፣ ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ክፍሎች እየተመራ ባለፉት የስራ ቀናት በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነራታ እና ቸርተከል ቀበሌዎች ተካሂዷል፡፡
በተጨማሪም በአዋበል ወረዳ የሰብል ስብሰባ ስራው የተከናወነ ሲሆን÷ በቀጣይ የስራ ቀናት የሰብል ስብሰባ ስራው በሌሎች የዘማች አርሶ አደሮች ማሳ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.