Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን 16 ሺህ አባ ወራዎች ከፀሐይ ብርሃን ሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚኖ ከተማ 16 ሺህ አባ ወራዎች ከፀሐይ ብርሃን ሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ። ከዞኑ ዋና ከተማ ሐረር ከ250 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው የሚኖ ከተማ አገልግሎት የጀመረው የፀሐይ ኃይል…

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፤ 80 በመቶ ተማሪዎችም ወደ ቀጣዩ ክፍል መዛወራቸው ተገልጿል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፤ 80 በመቶ ተማሪዎችም ወደ ቀጣዩ ክፍል መዛወራቸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን ቢሮው…

የጎርጎራ ፕሮጀክት የሚካሄድበት ስፍራ ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎርጎራ ፕሮጀክት የተሳለጠ እንዲሆን የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደር የፕሮጀክቱን ስፍራዎች ከሶስተኛ ወገን ነጻ እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው ጎርጎራ በአጭር ጊዜ ለማልማት የሚያስችለው ዝግጅት…

የአምባሳደር ስዩም ባለቤትና ልጃቸው ለህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የህክምናና የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር አለ መርማሪ ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትዳር አጋር ፈለገ ህይወት በርሄ እና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ለህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በድብቅ ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ እና በገንዘብ ሲደግፏቸው እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ገለጸ፡፡ ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ እንደሚካሄድ ተገለጸ። የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል። የመተከል ጉዳይ ዋነኛ…

በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቋመ። በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው እና…

ባለፉት 24 ሰዓታት 451 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 24 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 639 የላቦራቶሪ ምርመራ 451 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 1 ሺህ 24 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ…