Fana: At a Speed of Life!

ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍቢሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ባለፉት አምስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አስታወቁ፡፡ ባለፉት አምስት ወራት 1 ነጥብ 41 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ለማግኘት ታቃዶ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር…

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚገነዘብ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በጄኔቭ የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዋና ኃላፊ ፍራንሱዋስ ሚያንዳ መንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው የሕግ ማስከበር…

ወይዘሮ አዳነች በአዲስ አበባ በሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ሊዮ ዩሺ ጋር በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች እና ተያያዥ የትብብር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ። ምክትል…

ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር የሚኖራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ባስጠበቀ መልኩ ይቀጥላል – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር የሚኖራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትብብርና የጋራ ተጠቃሚነትን ባስጠበቀ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አምባሳደሩ የኢትዮጵያና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ…

ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ…

የመተከልን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህዝባዊ ውይይት በአሶሳ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከልን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህዝባዊ ውይይት ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተጀምሯል። በውይይት መድረኩ ከክልሉ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ውይይቱ የሀገር አቀፉ የማህበረሰብ…

የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሠላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የፀጥታ አካላት አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍቢሲ) ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሠላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የምስራቅ ኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት አስታወቁ፡፡ የሀረሪ ክልል፣ የድሬዳዋ አስተዳደር፣ የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች የፖሊስ ኮሚሽኖችና…

እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ ልታካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ወደ ጠቅላላ ምርጫ ልታመራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ምርጫው የሚካሄደው መንግስቱን የመሰረቱት ሁለቱ ፓርቲዎች በበጀት ጉዳይ ላይ ባለመስማማታቸው ነው ተብሏል፡፡ መራጮች ከ12 ወራት በኋላ በመጋቢት ወር…

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዩቫ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዩቫ ጋር ተወያዩ። በሀብታምና በደኻ መካከል የኑሮ ልዩነትን ስለ ማጥበብ እና በአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ አማካኝነት በአየር ንብረት ለውጥ…

ሁለተኛው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ውድድር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሁለተኛው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ውድድር ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ ዛሬ ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በሰጠው የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ውድድር ሊካሄድ መሆኑን ያስታወቀው፡፡ ውድድሩ በሦስት…