Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት የህግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ በስኬት መጠናቁን ገለጹ፡፡ አምባሳደር ነብያት ከአልጀሪያው ኤል ቻብ ጋዜጣ ጋር በትግራይ ክልል ከተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ሃገራዊ ጉዳዮች…

የደራሲና ተዋናይ ተ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደራሲና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሃፍትን የደረሱ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል። ዛሬ…

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 290 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ለ28ኛ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 3 ሺህ 290 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡ የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ…

የካናዳ አነስተኛ ንግድ እና ዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳ አነስተኛ ንግድ፣ የወጪ ንግድ ማስተዋወቂያ እና ዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሜሪ ኒግ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ አፍሪካና ኬኒያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። የሚኒስትሯ ጉብኝት የአፍሪካና ካናዳን የንግድ ዘርፍ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው…

በሚቀጥለው ወር ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደምትቀበል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምስራቅ አፍሪካዊቷ ኬንያ በቀጣዩ ወር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን እንደምትቀበል ገለጸች፡፡ የጤና ሚኒስትሩ ሙታሂ ካግዌ 24 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባት ማዘዛቸውን ነው የገለጹት፡፡ የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያው ዙር በወረርሽኙ ተጋላጭ የሆነ ዜጎች…

የመዲናዋን የመንገድ ሽፋን ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ጥናት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን የሚያሳድጉና የተቀላጠፈ የትራፊክ ፍሰት የሚፈጥሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እንዲያስችል ታሳቢ የተደረጉ የማስተር ፕላን የመንገድ ዲዛይን ጥናቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ…

ዶክተር ሊያ ከኳታር የህብረተሰብ ጤና ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከኳታር የህብረተሰብ ጤና ሚኒስትር ጋር ተወያዩ፡፡ ሁለቱ ሚኒስትሮች በውይይታቸው በጤናው ዘርፍ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የስምምነቱ አላማ በሀገራቱ…

በትምህርት ቤቶች ኮቪድን የመከላከል ስራው መጠናከር እንዳለበት ኮሚቴው አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሁለት ትምህርት ቤቶች ባደረገው የመስክ ምልከታ በመማር ማስተማር ስራው ኮቪድን አስቀድሞ ለመከላከል ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አሳስቧል፡፡…

የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ። ተጠርጣሪው ህውሓትና ኦነግ ሸኔ ከተባሉ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች…

ተቋርጦ የነበረው ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከብር ኖት ቅየራው ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረው ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር…