Fana: At a Speed of Life!

ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ዛሬ ንጋት ላይ መታየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ዛሬ ንጋት መታየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢኒስቲቲዩት አስታውቋል፡፡ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢኒስቲቲዩት እንዲሁም ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር የጨረቃ ግርዶሽ…

በደቡብ ወሎ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ ቀበሌ19 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 2ሰዓት ከመካነ-ሠላም ወደ መርጦለማሪያም 26 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ…

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸውን የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ፕሮሞሽን ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ይመር…

የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው። በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ ፋርማጆን ጨምሮ 39 ሰዎች በእጩነት ቀርበዋል። የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋውዚያ የሱፍ ሀጂ አደም ብቸኛዋ ሴት እጩ ሆነው…

በበቆጂ ከተማ በተካሄደ የታላቁ ሩጫ ውድድር አትሌት ደጀኔ ሃይሉና አትሌት መሰረት ሂርጳ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገ የታላቁ ሩጫ በ 7 ኪሎሜትር ውድድር በወንዶች አትሌት ደጀኔ ሃይሉ በሴቶች አትሌት መሰረት ሂርጳ አሸንፈዋል። “ኢትዮጵያ ትሮጣለች” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውድድር በአዋቂዎች 7 ኪሎ ሜትር ሩጫ፣…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ  በኢሲኤ  መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ የጉባኤው ዋና አላማ የተሻሻለውን የመተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ተናግረዋል፡፡…

በወራቤ ጉዳት የደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናትንና የንግድ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በቤተ እምነቶች ላይ የደረሰውን ውድመት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሙርሰል አማን እንዳሉት ÷የእምነት ተቋማቱን ገንብቶ ወደ…

የእሁድ ገበያ የመዲናዋን ነዋሪዎች በመደገፍ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የእሁድ ገበያ ነዋሪዎችን በመደገፍ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ካሉ ጉዳዮች አንዱ የእሁድ ገበያ…

መንግሥት ለክልሉ አርሶ አደሮች ከምርት እስከ ገበያ ትስስር ያመቻቻል -አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ፋፈን ዞን ደጋህሌ ከተማ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ዜጎች ለገበያ ያቀረቡትን ፍራፍሬ ጎብኝተዋል። የደጋህሌ ከተማ ለግብርና ምቹ ከሆኑ የክልሉ ከተሞች አንዷ ስትሆን አርሶ አደሮች…

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አመራሮች የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመለከቱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመልክተዋል። ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹና አመራሮቹ በሚኒስቴሩ…