Fana: At a Speed of Life!

ዋሊያዎቹ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ ኬንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን÷ ዋሊያዎቹ በበረከት ደስታና…

በኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃጸም ላይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ልኡክ ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) ልኡካን ቡድን አባላት ጋር ተወያተዋል፡፡ በውይይታቸው ኢትዮጵያ ተግባራዊ ባደረገችው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃጸም ዉጤቶች እና በቀጣይ…

የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።…

የአፍሪካ ሀገራት የጤና ድንገተኛና ፈጣን ምላሽ ዝግጁነት ኮሚቴ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የአፍሪካ ሀገራት የጤና ድንገተኛና ፈጣን ምላሽ ዝግጁነት ኮሚቴ ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ዘርፍ አመራሮችና የተለያዩ የልማት አጋሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ በጤናው…

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ሚሳኤል ወደ ሩሲያ አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዩክሬን ወደ ብሪያንስክ ግዛት ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች አምስቱ በሩሲያ ጦር የከሸፉ መሆኑን…

ኢትዮጵያ ለተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፤ ሶማሊላንድ በቅርቡ ባካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ…

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት መሳካት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የምክክር ሂደት እንደምታደንቅና ለሂደቱ መሳካት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ምክትል ረዳት ፀሃፊ ቪንሴንት ስፔራ ጋር…

በኦሮሚያ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ሃላፊ ጄነራል አበበ ገረሱ÷ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የነበረው የጸጥታ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ…

ደቡብ ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በዲጂታል ግብይት በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በዲጂታል ግብይት፣ በባህል ልውውጥና መሰል ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ያላትን ፍላጎት ገልፃለች፡፡ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ጁንግ ጋር…

በዴልሂ የተከሰተው የአየር ብክለት ከተማዋን ጨለማ አልብሷታል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ የተፈጠረው የአየር ብክለት ከተማዋን ጭጋግ በማልበስ ለእንቅስቃሴ አዳጋች ሁኔታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዴልሂ ከተማ የዓለም ጤና ድርጅት ለመተንፈስ አዳጋች ነው በሚል ካስቀመጠው የአየር ብክልት ደረጃ…