በኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ የ60 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ100 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ የ60 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
ጀልባዋ ከዋና ከተማዋ ኪንሻሳ በስተ ምሥራቅ በምሽቱ እየተጓዘች ከዓለት ጋር መጋጨቷን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡…