Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ፓርላማ አባል ክሪስሶላ ዛቻሮፖሉ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ እና የአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ፓርላማ የልማት ሐብት ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር እና የጋራ የፓርላማ ልዑክ ክሪስሶላ ዛቻሮፖሉ ጋር ተወያዩ፡፡…

በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች መደምሰሳቸውን ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች መደምሰሳቸውን በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አስታወቀ። በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉም…

አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ በታንዛኒያ ከሱዳን ኤምባሲ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫውን ታንዛኒያ ካደረገው የሱዳን ኤምባሲ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ የፌደራል መንግስት በክልሉ ህግ የማስከበር ስራ ለመስራት መገደዱን አስታውሰው ስለ ህግ ማስከበር ስራው…

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ…

በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የሃይል ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችንና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ 80 በመቶ ከሚሆነውና በግብርና…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን 3 ለ 2 አሸንፏል። ጌታነህ ከበደ የቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስቱን የድል ጎሎች በማስቆጠር ሐት ትሪክ ሰርቷል። የጅማ አባ…

የኦሮሚያ ክልል ከአፋርና ከሲዳማ ክልል በሚዋሰንባቸው ወረዳዎች የየክልሎቹን ቋንቋዎች ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል- አቶ አዲሱ አረጋ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ከአፋርና ከሲዳማ ክልል በሚዋሰንባቸው ወረዳዎች የክልሎቹን ቋንቋዎች በትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ…

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያስገነባቸውን ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያስገነባቸውን ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስመረቀ፡፡ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊትእመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር…

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ616 ሚሊየን 843 ሺህ ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ፣ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 5ኛ ዙር፣ 6ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ከ616 ሚሊየን 843 ሺህ ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እና የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል፡፡…

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርሾን ጋር ተወያዩ፡፡ ውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከር ዓላማው ያደረገ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ…