Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ 112 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በፃግብጂ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ቤት በተካሄደ ፍተሻ 110 ሺህ ባለ ሁለት መቶ ብር እና 2ሺህ ባለ መቶ ብር በድምሩ 112 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖት መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፓሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዋና…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና 3ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ አቡበከር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና ሶስቱንም ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ የሰራ ሲሆን፤ በሲዳማ ቡና በኩል መሃሪ መና፣ ማማዬ ሲዲቤ እና ይገዙ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቀጣይ 3ወራት ተግባራት ዙሪያ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀምሯል፡፡ በሀገራዊ ጉዳዮች እና በቀጠና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና ከክልል አመራሮች ጋር የሚካሄድ የሁለት ቀናት ስብሰባ ዛሬ መጀመሩን…

አቡበከር ናስር የፕሪምየር ሊጉን የግብ አግቢነት ሪከርድን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አቡበከር ናስር በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል የማስቆጠር ሪከርድን ሰብሯል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ላይ 9ኛ፣ 36ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሮ የውድድር ዘመኑ ጎሎቹን ቁጥር 27 አድርሷል፡፡ በዚህም…

ጊዜያዊ የመራጮች ምዝገባ መረጃ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እስካሁን ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከ36 ሚሊየን 245 ሺህ በላይ ሰዎች ተመዝግዋል፡፡ በዚህም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ማለትም በአዲስ አበባ 1ነጥብ451 ሺህ 790ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 177ሺህ 519 ሰዎች…

አስትራዜኒካ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተከትበዋል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አስትራዜኒካ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች መከተባቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው እንደገለጹት በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለውን ክትባት በየደረጃው…

በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ዝርያ አሳሳሳቢ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል – የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ዝርያ አሳሳሳቢ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አሳሰበ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ቫይረስ አሳሳሳቢ ዝርያ እንደሆነ እና ዓለም አቀፍ ስጋት…

ዶ/ር አብርሃም በላይ አሸጎዳ የሚገኘውን የትራክተሮች መገጣጠሚያ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አሸጎዳ በሚገኘው የትራክተሮች መገጣጠሚያ ጉብኝት አካሄዱ። በጉብኝቱ ወቅትም፥ የክልሉ የግብርና ስራ ወደ ነበረበት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት በቴክኖሎጂ የታገዘ እርሻ…

የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመላው ሃገሪቱ ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ እንሚጠናቀቅ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣…

ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከ432 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከ432 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በሚኒሊክ አደባባይ…