Fana: At a Speed of Life!

ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡና ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን ማከናወን ይገባል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡና ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ100 ቀን የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እየተካሄደ…

ፌዴራል ፖሊስን መቀላቀላችን ለላቀ ሀገራዊ ኃላፊነትና የህዝብ አገልግሎት እንድንዘጋጅ አድርጎናል – የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌዴራል ፖሊስን መቀላቀላችን ለላቀ ሀገራዊ ኃላፊነትና የህዝብ አገልግሎት እንድንዘጋጅ አድርጎናል ሲሉ የቀድሞ የክልሎች ልዩ ኃይል አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ወደ…

በመጭው ክረምት 1 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በሩዝ ምርት ይሸፈናል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በመጭው ክረምት 1 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በሩዝ ምርት እንደሚሸፈን አስታወቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ከሁለት አመት በፊት አዲስ የሩዝ ልማት ከ7 ሺህ ሄክታር…

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም በስነ-ምግብ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ልዑክን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው…

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ብሄራዊ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ብሄራዊ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡ በኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራው የልዑካን ቡድን ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋርም ተወያይቷል፡፡ በነበራቸው…

የዓለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ባንክ የፋይናንስና የግል ሴክተሮች ፕራክቲስ ሃላፊ አልዋሊድ አላባታኒ የተመራ ልዑክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የማሽን ኪራይ ብድር ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኘ፡፡ በጉብኝቱ ላይ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣…

የዓለም ሙቀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊያልፍ እንደሚችል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ቢያንስ አንዱ አመት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሞቃታማ እንደሚሆን የዓለም የአየር ትንበያ ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የሙቀት አማቂ ጋዞች እና ኤልኒኖ በመጣመር የሙቀት መጠኑን እየጨመሩ በመሆኑ÷ ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት…

ኢትዮጵያና ኮሎምቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ በፖለቲካ ምክክርና በሌሎች የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። አገራቱ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸውንም አስታውቀዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር…

3ኛው የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት የሚኒስትሮች ስብስባ በጁባ መካሄደ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት የሚያስተሳስረው የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት የሚኒስትሮች ስብስባ በጁባ መካሄደ ጀመረ፡፡ ስብሰባው “ፈጣን የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት ትግበራ ለሰላም፣ ለእድገት፣ ለዘላቂ  ልማትና ለቀጣናዊ ትስስር" በሚል መሪ…

ፍርድ ቤቱ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም 10 ቦምቦችን ደብቀው ተይዘዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ወንጀል ለመፈፀም በማሰብ 10 ቦምቦችን በቤት ውስጥ ደብቀው ተይዘዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ። ሕገ -መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በኢ-መደበኛ አደረጃጀት የሽብር ወንጀል ለመፈፀም…