ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አልባሳት ግዢ ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና አቅርቧል የተባለው ስራ አስኪያጅ በሙስና ወንጀል ተከሰሰ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ አልባሳት ግዢ ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና አቅርቧል የተባለው ስራ አስኪያጅ በሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡…