Fana: At a Speed of Life!

በ60 ሚሊየን ብር ወጪ መልሶ የተገነባው የመጠጥ ውሃ ተቋም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ብሔራዊ ክልል ጨርጨር ወረዳ በጦርነቱ ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበረው የውሃ ተቋም አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በምረቃ መርሐ-ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ÷ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የፌደራል መንግስት በጦርነት…

የተጭበረበረ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጡ ተከሳሾች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 500 ካሬ ሜትር ቦታ የተጭበረበረ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጡ 8 ተከሳሾች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጡ፡፡ ተከሳሾቹ የቀድሞ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ ሁለት የወረዳው የመሬት ልማት ባለሙያዎችና…

ጀርመን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ስራዎች እንዲሳኩ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፍን ኡር ጋር ተወያዩ ። አምባሳደር ተሾመ÷ የተሃድሶ ኮሚሽን የተቋቋመበትን ዓላማ፣ እስከ አሁን የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና ከልማት አጋሮች…

ጠፍቷል የተባለው የዩራኒየም ክምችት መገኘቱን ሊቢያ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠፍቷል የተባለው የዩራኒየም ክምችት መገኘቱን የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ቃል አቀባይ ጀነራል ካሊድ ማህጁብ ገልፀዋል፡፡ ዩራኒየሙ የተገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኒውክሌር ኤጀንሲ መጥፋቱን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡…

ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ተግዳሮቶች የሀገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደጎዱት ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ችግሮችን ተከትሎ የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱ ተገለፀ። የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዘርፍ እየፈተኑ ባሉ ተግዳሮቶች ላይ መፍትሄ ለማምጣት ያለመ ውይይት ከባለ ድርሻ…

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ…

የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም በስርዓተ-ፆታና ዳያስፖራ ተሳትፎ ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛው የምስራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም የቴክኒካል የሥራ ቡድን በስርዓተ-ፆታ እና ዳያስፖራ ተሳትፎ ላይ እየመከረ ነው፡፡ በምክክሩም ሀገራት በስርዓተ-ፆታ እና ዳያስፖራ…

የማዳበሪያ ግዥ ላይ 21 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓል-ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2015/16 የመኸር ወቅት የማዳበሪያ ግዥ ላይ 21 ቢሊየን ብር ድጎማ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተያዘው የመኸር ወቅት የማዳበሪያ ግብዓትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የግብርና…

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለጋራ ጥቅም በቅርበት ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ ናት – የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለጋራ ጥቅም በቅርበት ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ ናት ሲሉ የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ተናገሩ፡፡ በቻይና የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ…

በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አሰባስበው ያስረከቡ አካላት አስፈላጊውን ሰነድ በመያዝ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያክልል መንግስት በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አሰባስበው ያስረከቡ እና በማሰባሰብ ላይ ያሉ አካላት አስፈላጊውን ሰነድ በመያዝ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ክልሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት÷በአንዳንድ ዞኖች በድርቅ…