Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ በ18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ስምንት መንገዶችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በ18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ስምንት መንገዶችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈራረመ። በዛሬው ዕለት ስምምነት የተፈረመባቸውን መንገዶች ጨምሮ በ2013 ስድስት ወራት ብቻ በ43 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነቡ 21 የመንገድ…

በትግራይ ክልል የሰላማዊ ዜጎች ሞትን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች ያልተረጋገጡና ካልተሳካ የፖለቲካ ፍላጎት የተነሳ የሚለቀቁ ናቸው -መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሰላማዊ ዜጎችን ሞት በተመለከተ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚወጡ መረጃዎች ያልተረጋገጡና ካልተሳካ የፖለቲካ ፍላጎት የተነሳ የሚለቀቁ መሆናቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው አስታወቀ። መረጃ ማጣሪያው ባወጣው መግለጫ…

በጋምቤላ ክልል በቀጣይ አሥር ዓመታት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ እቅድ ተዘጋጅቷል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በቀጣይ ዐሥር ዓመታት ውስጥ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ እቅድ መዘጋጀቱን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ። በክልሉ የዐሥር ዓመት መሪ የልማት እቅድ ላይ የክልሉ…

ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ 46 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ የንግድ እና የማምረቻ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባካሄደው ክትትልና ቁጥጥር ህግ ተላልፈው በተገኙ 46 ድርጅቶች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ…

የሰላም ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስቴቨን ኦማሞ ጋር ተወያዩ፡፡ ሚኒስትሯ የዓለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ ቀውስ ባጋጠማት ወቅት ሁሉ ከኢትዮጵያ ህዝብና…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የድጋፍ ሰልፎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተካሄዱ፡፡ የድጋፍ ሰልፎቹ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በጉጂ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እንዲሁም በቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች ነው የተካሄዱት፡፡ ከዚህ ባለፈም በአምቦ፣ ለገጣፎ፣…

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት መካከል 91 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎች ወደ ወደ 9ኛ ክፍል ተዛወሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትምህርት የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን የቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ አስታወቁ። በዚህም በሲዳማና በደቡብ ክልል ለፈታና ከተቀመጡ 352 ሺህ 806 ተማሪዎች ውስጥ ወደ 322 ሺህ 136 የሚሆኑት…

337 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ ወደ አገር የተመለሱትን ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ…

የፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ኮሚሽነርነት የምረጡኝ ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ኮሚሽነርነት የምረጡኝ ዘመቻ መርሃግብር ተካሄደ። በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ህብረት…

የሶማሊያ መንግስት የደቡብ ምዕራብ ክልል ልዑክ በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች ሁኔታ እና በሰላምና ፀጥታ ላይ ለመምከር ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ መንግስት የደቡብ ምዕራብ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊ ልዑክ በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ሃይሎች ሁኔታ እና ከሶማሌ ክልል መንግሥት ጋር በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለመወያየት ጅግጅጋ ገባ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ሃላፊና…