Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ትዝታ ለህንድ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ለህንድ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ሰላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ማብራሪያ ሰጡ። በህንድ የኤክስፖርት ድርጅት የተዘጋጀና ከኮቪድ 19 በኋላ በኢትዮጵያና ህንድ ያለው የንግድና…

የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን የመተካት ሙሉ አቅም እንዳላቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን የመተካት ሙሉ አቅም እንዳላቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሸቴ አስፋው ተናግረዋል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአማራ…

ኤፍ ቢ አይ የታጠቁ የትራምፕ ደጋፊዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ታጣቂ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ጆ ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው በፊት በመላ አሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ። የታጠቁ ቡድኖች ከስምንት ቀን በኋላ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት…

የአጊቱ ጉደታ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…

በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ እና ላሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማት ምስጋና ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ'ገበታ ለሀገር' ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሠኝ በመላክ ያሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማትን ይፋ አደረገ:: ጽሕፈት ቤቱ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ እና ደረሠኙን በመላክ ላሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማት ምስጋና…

ስዊድን የኢትዮጵያን የሪፎርም ስራዎች እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ሉንድኪስት ጋር ተወያዩ። ሚኒስትሯ የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ሴቶችና ህጻናት፣ ሰላም ግንባታ ዘርፎች እንዲሁም በአጠቃላይ የሪፎርም ጉዞ ላይ…

የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ። በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጁንታው ነፃ በማድረግ የሕግ…

በቡራዩ 4 የእጅ ቦምብ እና 1 ፈንጂ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቡራዩ ከተማ አስተዳደር 4 የእጅ ቦምብ እና 1 ተቀጣጣይ ፈንጂ ተያዘ። ህገወጥ የጦር መሳሪያው በህብረተሰቡ ጥቆማ በገፈርሳ ቡራዩ ቀበሌ ነው የተያዘው። ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ህገወጥ የጦር መሳሪያው መገኘቱን አስታውቋል።…

8 ሺህ 370 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ታዳሽ ሃይል ማመንጨት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች በስራ ላይ ናቸው- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረገች መሆኗን የኢፌዴሪ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር…

የትግራይ ክልልን መልሶ የማቋቋም መርሐ-ግብር ተነድፎ ወደ ተግባር ተገብቷል፦ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት በትግራይ ክልል የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ መጠናቀቅን ተከትሎ በአፋጣኝ የመልሶ ማቋቋም መርሐ ግብር በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። በቅርቡ ከተለያዩ…