Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ በጎዴ  እና በአሶሳ ከተሞች ስም ትምህርት ቤቶች ተሰየሙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሶማሌ ክልል ከተማዋ ጎዴ  እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ዋና ከተማ አሶሳ ስም ትምህርት ቤቶች ተሰየሙ። ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ፣የአዲሰ አበባ ምክር ቤት…

ህዝቦች በአንድነት፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እንዳይኖሩ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ የቆየው የጁንታው ቡድን ላይመለስ ፈራርሷል፡- ብልፅግና ፓርቲ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረ ብሄራዊ አንድነት ሁሌም ያሸንፋል ሲል የብልፅግና ፓርቲ ፓርቲ አስታወቀ። የብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው በሀገሪቱ ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል የህዝቡን እውነተኛ የዴሞክራሲ ጥያቄ ለመመለስ እና…

የትግራይ ህዝብ በአንድ አጥፊና ካሃዲ ቡድን መገለፅና መወከል እንደማይፈልግ በተግባር አስመስክሯል- የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ህዝብ በአንድ አጥፊና ካሃዲ ቡድን መገለፅና መወከል እንደማይፈልግ በተግባር አስመስክሯል ሲል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታወቀ። በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት  ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው…

ከተማረክንም በህወሃት ጁንታ ሳይሆን በኢትዮጵውያን እና በኢትዮጵያዊነት ነው- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያካሄደ የነበረውን ህግን ማስከበር ዘመቻ አጠናቆ እና ህዝቡን በማረጋጋት ወደ ቀየው መመለስ መጀመሩን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ። የራያ ግንባር አዛዥ ሌተናል  ጄኔራል ባጫ ደበሌ ህግን…

የጁንታው ቡድን በመሸነፉ ህዝቡ ደስታውን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህግ ማስከበር ዘመቻው የጁንታው ቡድን በመሸነፉ ህዝቡ ደስታውን ገለጸ። የባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮሶበር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ዳንሻ፣ ወልድያ፣ ቆቦ እና የሌሎች ከተማ ነዋሪዎች የህወሓት ጁንታ በመሸነፉ ደስታቸውን…

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ወይዘሮ አዳነች “የድል አርማ የሃገር ደጀን የህዝብ ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በተቀዳጀው…

ህግ የማስከበሩ ምዕራፍ በድል ተጠናቋል በመጭው ጊዜ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀን አንዘናጋ -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። “ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ የመከላከያ ሀይላችን ላጎናጸፈን ክብር መላው ኢትዮጵያውያንን እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል፡፡…

ምክር ቤቱ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል የተሰማውን ደስታ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል የተሰማውን ደስታ ገለፀ። ምክር ቤቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደሰ አላችሁ ብሏል። የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ላሳየው…

መስዋዕት ሆነው ኢትዮጵያን ወደፊት ላራመዱ ታሪክ ሰሪዎች ክብር ይገባል – ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መስዋዕት ሆነው ኢትዮጵያን ወደፊት ላራመዱ ታሪክ ሰሪዎች ክብር እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ። ሚኒስትሯ በህወሓት ጁንታ ላይ የተመዘገበውን ድል አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችው መልዕክት አስተላልፈዋል።…

ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው። አቶ ገዱ የህግ የበላይነት ዘመቻ ድልን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት…