Fana: At a Speed of Life!

ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉት የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የዝግጁነት አቋም ላይ ይገኛሉ- ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉትን የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የዝግጁነት አቋም ላይ እንደሚገኙ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ገለፁ። ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በዛሬው እለት መግለጫ…

በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ታጣቂዎች ልዩ ኃይሉና ወጣቱ የጥፋት ቡድኑ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ልዩ ኃይሉና ወጣቱ የጥፋት ቡድኑ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሆን የለባቸውም ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ገለጹ። ከአንድ ሳምንት በፊት በትግራይ ክልል በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ቡድን…

የህወሓት አጥፊ ቡድን ዛሬም በማጭበርበር ተግባሩ እርስ በእርሱ በተጣረሱ የእያሸነፍን ነውና የእንደራደር ሀሳቦችን እየሰነዘረ ነው- አቶ ነቢዩ ስሁልሚካኤል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት አጥፊ ቡድን ዛሬም የማጭበርበር ተግባሩን እርስ በእርሱ በተጣረሱ የእያሸነፍን ነውና የእንደራደር ሀሳቦችን እየሰነዘረ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል ገለፁ። አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል ከፋና…

የሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል፣ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ደም ለግሰዋል። በዚህም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ…

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊው ግብዓት ይሟላል- ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት በሁሉም ወረዳዎች በሚፈለገው መንገድ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊው ግብዓት እንደሚሟላ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ። የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ…

በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል። በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት…

የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትን እና ለሌሎች ፀጥታ አካላትን ለመደገፍ የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ እያደረጉ ይገኛል:: ከ200 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች በበጎ ፍቃድ ደም የለገሱት…

የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ፡፡ መስታወታቸው ረግፏል፤ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ኃይል ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አስታወቀ። ታጣቂ ቡድኑ የህዝብን ሠላም ለማደፍረስና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች…

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ችቦ በጅግጅጋ ከተማ ተለኮሰ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ለሚከበረው 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ተለኩሷል። በችቦ የመለኮስ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ…