Fana: At a Speed of Life!

በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ 4 ሺህ 183 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ 4 ሺህ 183 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሁሴን ዑስማን እና…

ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ100 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን በዛሬው ዕለት የ100 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር ተፈራርመውታል። የተፈረመው ስምምነት…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በፕሮፌሰር መስፍን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ። ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን የፓለቲካ ምህዳር አንጋፋ ቦታ የነበራቸው ፣ ሃሳባቸውን ካለ…

ብሪታንያ እና ካናዳ በቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ላይ እገዳ ጣሉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ እና ካናዳ በቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ላይ እገዳ ጣሉ፡፡ ሃገራቱ በፕሬዚዳንቱ ላይ በሃገሪቱ ከተካሄደው ምርጫ እና እሱን ተከትሎ በተቃዋሚዎች ላይ ተፈጽሟል ከተባለው የሃይል እርምጃ ጋር ተያይዞ የጉዞ እና ንብረታቸው…

በአማራ ክልል የ2012 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች 70 በመቶ ተጠናቀዋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል የ2012 በጀት ዓመት የካፒታል  ፕሮጀክቶች 70 በመቶ መጠናቀቁን  የክልሉ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ገለፀ። የክልሉ የ2012 ዓ.ም የካፒታል ፕሮጀክቶች የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ዛሬ ባህርዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡…

ዘለፋ የበዛበት የዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን የፊት ለፊት ክርክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀደሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለህዳሩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ንጋት ላይ የፊት ለፊት ክርክር አድርገዋል። ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን በህዳር ወር የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማሸነፍ…

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ በፕሮፌሰር መስፍን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ። ርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮፌሰር መስፍን ትልቅ የእውቀት አባት፣ ቁርጠኛ ሰላማዊ ታጋይ፣ የሰብዓዊ መብት…

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ ሆኖ ከሰንደቅ አላማና መለዮ ጋር በመርህ የሚሰራ ሰራዊት ለመገንባት የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላል – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ ሆኖ ራሱን ከሰንደቅ አላማና መለዮ ጋር ሁልጊዜ በመርህ የሚሰራ ሰራዊት ለመገንባት የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፌደራል ፖሊስ…

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የጂኦግራፊ መምህር፣ ፖለቲከኛ፣ ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም በፕሮፌሰር መስፍን እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።…

የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል  

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ የጋራ ስብሰባ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚያካሂዱ ተገለፀ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ሰብሰባውን አስመልክቶ…