Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕና ባለቤታቸው ሜላኒያ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ፡፡ ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንቱና ባለቤታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡ ይህ የተሰማው የቅርብ ረዳታቸው የሆነ ሰው በኮሮና…

በአዲስ አበባ የ13ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኞችና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ቁልፍ ርክክብ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የ13ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ዛሬ ካርታ፣ ቁልፍ እና ውል ርክክብ በይፋ ተጀመረ። በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ ባለው መርሃ ግብር 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች እና…

የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡ የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ዶክተር ማተቤ ታፈረ እንደገለፁት አካዳሚው የሰው ሀይል፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የማስተማሪያ ክፍሎች፣ የማሠልጠኛ እና የመኝታ አገልግሎት…

የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ፖሊሲ እንዲሁም የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ። የብሄራዊ ትራንስፖርት ፖሊሲ፣ የሎጅስቲክስ ዘርፍ ፖሊሲ እና የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን የሚመለከት መርሀ ግብር እየተካሄደ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ዜጎች የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዜጎች የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባሳለፍነው የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ላይ ለሚገኙት ሁሉ አድናቆታቸውን…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያዩ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ የተመራ የልዑካን…

ባለፉት 24 ሰዓታት 784 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 139 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 784 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 75 ሺህ 368 ደርሷል።…

ሀገራዊ ትውፊቶች በአግባቡ ሊጠበቁ እና ለትዉልድ ሊተላለፉ ይገባል-የባህል እና ታሪክ ተመራማሪዎች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሃገራዊ ትዉፊቶች በአግባቡ ሊጠበቁ እና ለትዉልድ ሊተላለፉ እንደሚገባ የባህል እና ታሪክ ተመራማሪዎች ተናገሩ ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና ከሚያቀርብባቸው ስነ ስርዓቶች ውስጥ አንዱ  የኢሬቻ ክብረ በዓል ነው ፡፡ ከዝናባማው …

የኢትዮጵያ መንግስት በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ሱዳናዊያን የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ሱዳናዊያን የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ አደረገ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በጎርፍ ለተጎዱ ሱዳናዊያን የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ለማድረግ…

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለፈው በጀት አመት ከታክስ በፊት 55 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር አተረፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ያሉ 21 የልማት ድርጅቶች በ2012 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 55 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር አተረፉ፡፡ ትርፉ በበጀት ዓመቱ ከተሰጠ የ300 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ምርትና አገልግሎት…