Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአስቸጋሪ ወቅት በየመኖሪያ አካባቢ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በቅርበት መደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስገንዝበዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው…

የኮቪድ19 ስርጭት መስፋፋት ከቀጠለ የምርት አቅርቦት ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር አማራጭ ስትራቴጂ ተዘጋጅቷል – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮቪድ19 ስርጭት መስፋፋት ከቀጠለ የምርት አቅርቦት ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር መንግስት አማራጭ ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ። የኮቪድ19 በመላው ዓለም በሰው ልጆች ጤና ላይ ካደረሰው…

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ የላትም” ጠ/ሚ/ር ሀምዶክ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ከሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሀገራቸው ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ የላትም ሲሉ ተናገሩ፡፡   እንደ አል ዐይን ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት…

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማዕከልነት እየተዘጋጀ መሆኑን የአካዳሚው የውድድር እና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ አብዮት ተስፋዬ ተናገሩ። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ወደ ጊዜያዊ የኮሮና ቫይረስ…

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 1 ሺህ 300 ንጹሃን ተገድለዋል – ተመድ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 1 ሺህ 300 ንጹሃን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ በተወሰኑ ወራት ውስጥ በሃገሪቱ ሶስት የተለያዩ ግዛቶች በተቀሰቀሰ ግጭት ሳቢያ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን አስታውቋል። ከዚህ…

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ1 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 798 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው። ቫይረሱ የተገኘባቸው እድሜያቸው ከ1 እስከ 78 አመት የእድሜ ክልል የሚገኝ ሲሆን፥ 111 ወንድ እና 58 ሴቶች ናቸው። ከዚህ…

ኤጀንሲው በለይቶ ማቆያ ለሚገኙ ሰዎች 6 ሺህ መጽሐፍት ለገሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና መጽሐፍት ኤጀንሲ በለይቶ ማቆያ ለሚገኙ ሰዎች የሚሆኑ 6 ሺህ መጽሐፍትን ለጤና ሚኒስቴር ዛሬ ለገሰ። መጽሐፍቱ በተለያዩ ዘውጎች የተጻፉ ሲሆኑ፥ ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገቡ ሰዎች በቆይታቸው ወቅት ራሳቸውን…

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአረንጓዴ አሻራ ቀን መልዕክት

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ላለፉት ጥቂት ወራት ዓለም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ፈተና ውስጥ ገብታ ቆይታለች። የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ሁላችንም ኃላፊነታችንን በመወጣት ላይ እንገኛለን። ይህ ጊዜ እንድናውቅ ያደረገን አንድ ነገር ቢኖር የሰውን ልጅ ተጋላጭነት፣ የግል ጤንነትን የመጠበቅ…

የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ጎን ለጎን ደም የመለገሱ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ጎን ለጎን ደም የመለገሱ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጥሪ አቀረቡ። የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በብሔራዊ ደም ባንክ በመገኘት ደም ለግሰዋል። ዶክተር ሊያ…

ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው። የአረንጓዴ አሻራው ቀን በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወንጪ ወረዳ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ…