Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የ3 ሺህ 757 የላብራቶሪ ምርመራ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ…

የመዲናዋ ካቢኔ የታክስ ጫና ማቃለያ እና ውዝፍ እዳ ስረዛ እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡ በዚህም ከ1997-…

በጀርመን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ርቀትን በመጠበቅ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች በሯን ክፍት አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በርሊን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ በአንድ መስጅድ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች እንዲጠቀሙ ፈቅዳለች። ፈቃዱ የተሰጣቸው በበርሊን በሚገኘው ዳር አሳላም መስጅድ የሚፈለገውን ያህል ርቀት በመጠበቅ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን…

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና ከንቲባዎች የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት እያስተላለፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና ከንቲባዎች የ1441ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ። የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ልዩ…

ህብረቱ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን አወደሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት ኢትይጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቴክኒክ ደረጃ የሚያደርጉትን ድርድር ለመቀጠል መስማማታቸውን አወደሱ። ሊቀ መንበሩ ሃገራቱ በህዳሴው ግድ ዙሪያ ከሰሞኑ ያሳዩትን አቋም…

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ1 ሺህ 441ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ ባስተላፉት መልዕክት “ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወገኖቼ መልካም…

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ማዘጋጀቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ማዘጋጀቱን ገለፀ። የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳእየሁ እንደገለፁት፥ በክልሉ ለችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።…

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዒድ አልፈጥር መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለእስልምና አምነት ተከታዮች የ1441ኛው የዒድ አልፈጥር ክብረ በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ። አቶ ደመቀ በመልዕክታቸው “በዘንድሮው ታላቁ የረመዳን ወር በፆም የዘለቅነው ሲሆን፥…

በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው በተጨማሪ በአማራ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላቦራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በክልሉ ለ41 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ አራት ሰዎች…