Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን 2 የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አወጣ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በዛሬው እለት ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አውጥቷል። ባለሥልጣኑ የፈቃድ አሠጣጥ ሂደቱን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ በተሠጠው ሥልጣን መሠረት እየመራ ሲሆን ይህም…

በሕዳሴ ግድብ ዙርያ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙርያ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ ተደርጓል። በመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው መድረክ ላይ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ…

አቶ ታደሰ ካሳ በሌላ የክስ መዝገብ 8 ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ በሌላ የክስ መዝገብ 8 ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ። ችሎቱ ቅጣቱን ያሳለፈው ጥረት ኮርፖሬትን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ይመራ…

በ24 ሰዓት በተደረገ 3 ሺህ 747 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 747 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 398 መድረሱን…

በአዲስ አበባ ተሰብስበው ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው እስከ 20 ሺህ ብር ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው በመሰባሰብ ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 20 ሺህ ብር እና በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ። የየክፍለ ከተማው…

በአዲስ አበባ በአመራርነት የሚሰሩ የትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እስከ ወረዳ በአመራርነት የሚሰሩ የትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ውይይት አካሄዱ።   በኮቪድ-19 ምክንያት የምርጫ መራዘም እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው ውይይቱን ያካሄዱት።…

የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የጤና ሚኒስቴርና የምርጫ ቦርድ የባለሞያዎችን ማብራሪያ አደመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የህገ መንግስት ትርጉምን በተመለከተ ያዘጋጀው የባለሙያዎች ሀሳብ መስጫ ተካሂዷል። በዛሬው እለትም የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡትን የባለሞያዎች…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለኢትዮጵያ የመመርመሪያ ኪቶችን ለላከው ለቴንሴንት ፋውንዴሽ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ የመመርመሪያ ኪቶችን ለላከው የቴንሴንት ፋውንዴሽኑ ማ ሁዋንቴንግን ምስጋና አቀረቡ። ቴንሴንት ፋውንዴሽ ለኢትዮጵያ የላካቸው የኮሮናቫይረስ የመመርመሪያ ኪቶች አዲስ አበባ ደርሰዋል። ይህንን…

በዓለም ላይ በአንድ ቀን ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለማችን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በትናንትናው እለት ብቻ በዓለማችን ላይ 106 ሺህ አዲስ የኮሮና…

የኮሮናቫይረስ በአንድም የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት በሚገኝ ታራሚ ላይ አለመገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ በአንድም የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት በሚገኝ ታራሚ ላይ አለመገኘቱን የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው፥ ኮቪድ-19 በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝ በአንድ በፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና…