Fana: At a Speed of Life!

      ጎግል አዋኪ ያላቸውን 600 መተግበሪያዎች አገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል አዋኪ ያላቸውን 600 መተግበሪያዎች ማገዱን አስታወቀ። ጎግል ከፕሌይ ስቶር ከተወገዱት 600 የአንድሮይድ መተግበሪያዎች ጋር ተያይዞ ተጠቃሚዎች ማስታወቂዎችን ክሊክ እንዲያደርጉ ክትትል የሚያደርጉ የመተግበሪያ አበልፃጊዎችንም አግዷል።…

አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከ29 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያጡ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር አየር መንገዶች በፈረንጆቹ 2020 በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 29 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር እንደሚያጡ አስጠነቀቀ። ማህበሩ ከአስር ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል…

ወጣት ስራ አጥ ሀኪሞችን ቁጥር ለመቀነስ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣት ሀኪሞችን በማብቃት የጤና አገልግሎቱን ማጎልበት በሚል መሪ ቃል 56ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ወጣት ስራ አጥ ሀኪሞችን…

የቤት ውስጥ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ጨቅላ ህፃናትን ለአስም እንደሚያጋልጡ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህፃናት ልጆችን ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ ማሳደግ ዋነኛው የቤተሰብ አላማ እና ፍላጎት ነው። ልጆች በጉንፋን እና ሌሎች ተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ የቤት ውስጥ የንፅህና መጠበቂያዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋል። ሆኖም በቤት ውስጥ ጥቅም ላይ…

የአሜሪካ የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ጥቃት ደረሰበት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ የበይነ መረብ ጥቃት ሰለባ መሆኑ ተገለጸ። ኤጀንሲው የሃገሪቱ ትላልቅ ወታደራዊ ግንኙነቶችን ጨምሮ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን የሚከታተልና የመረጃ ደህንነት ስርአቱን የሚቆጣጠር ነው።…

ሀዋሳና ቢሾፍቱን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀዋሳና ቢሾፍቱን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ስራ በመደገፍ የተለያዩ የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይ በርካታ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ በደቡብ…

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ተገለፀ። አቶ አሸብር በቀድሞ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተቀበሉ ሲሆን፥ ከብሪታንያ ግሪንዊች…

የግብርናውን ዘርፍ በቀጣይ ማዘመን የሚያስችል ስትራቴጂክ አማራጭ ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብርናውን ዘርፍ በቀጣይ ማዘመን የሚያስችል ስትራቴጂክ የአማራጭ ጥናት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆነ። ጥናቱን የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው ያካሄዱት። ይህ ጥናት በተለያየ ጊዜ…

ቲክ ቶክ አዲስ የደህንነት መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲክ ቶክ አዲስ የደህንነት መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ ነው። ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው ቲክ ቶክ ወላጆች ልጆቻቸው የሚጠቀሙትን የማህበራዊ ትስስር ገጽ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል አዲስ የደህንነት መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ መሆኑን ገልጿል።…

አትሌት አባብል የሻነህ በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ከሂማህ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች። አትሌት አባብል በፈረንጆቹ 2017 ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ በቫሌንሺያ…