Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
ናይጄሪያ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውጭ ምግብ የምታስመጣበት ገንዘብ የላትም-ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ችግር አገሪቱ ከውጭ ምግብ የምታመጣበት ምንም ገንዘብ እንደሌላት ገለጹ ፡፡
ስለሆነም አርሶ አደሮች አገሪቱን ለመመገብ የሚያስችል በቂ ምርት ማምረት አለባቸው ብለዋል…
የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስን ለማከም ይረዳል በተባለው ሃይድሮክሲክሎሮኪን የወባ መድሃኒት ላይ የሚያደርገውን ሙከራ አቋረጠ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስን ለማከም እንደሚረዳ የተነገረው ሃይድሮክሲክሎሮኪን በተባለው የወባ መድሃኒት ላይ ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ አቋረጠ።
ሙከራው የተቋረጠው መድሃኒቱ ከደህንነት ጋር ተያይዞ አደጋ ሊያደርስ ይችላል በሚል ስጋት…
ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳቷን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺዞ አቤ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግባቸው የነበሩ አከባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ ተነስቷል ሲሉ ነው ይፋ…
አውስትራሊያ ከወራት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ሰደድ እሳት ጉዳይ ላይ ምርመራ ጀመረች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ባለፈው መስከረም ወር ተቀስቅሶ በነበረው ሰደድ እሳት ጉዳይ ላይ ምርመራ ጀመረች።
የሰደድ እሳት ጉዳዮችን የሚመለከተው ኮሚሽንም ረጅም ጊዜ የሚወስደውን ምርመራ በዛሬው እለተ መጀመሩን አስታውቋል።
በምርመራው የደረሰው አጠቃላይ…
አሜሪካ ከብራዚል የሚመጡ መንገደኞች እንዳይገቡ እግድ ጣለች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋሽንግተን ከብራዚል ወደ አሜሪካ በሚገቡ የውጭ ሃገር ተጓዞች ላይ እገዳ ጣለች።
እገዳው የአሜሪካ ዜጎችን የማይመለከት ሲሆን ላለፉት 14 ቀናት በብራዚል ቆይተው ወደ አሜሪካ በሚገቡ የውጭ ሃገር ተጓዦች ላይ የተጣለ ነው ተብሏል።
የአሁኑ…
ዶ/ር ቴድርስ አድሃኖም መልካም ስራ ሰርተዋል- ቻይና
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዙሪያ መልካም ስራ መስራታቸውን ቻይና ገለፀች።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በቻይና ብሄራዊ ኮንግረስ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የዓለም ጤና…
ሱዳን የህክምና ባለሙያዎቿን ከጥቃት የሚጠብቅ የፖሊስ ኃይል ልታቋቁም ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን የህክምና ባለሙያዎቿን ከጥቃት ለመጠበቅ የፖሊስ ኃይል ልታቋቁም መሆኗን ገለጸች።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መባባሱን ተከትሎ በጤና አጠባበቅ ሰራተኞቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የፖሊስ ሃይል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ…
በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ከአውፓውያኑ መጋቢት ወር ማገባደጃ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና በአንድ ቀን የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በኒው ዮርክ በ24 ሰዓት 84 ሰዎች ሲሞቱ ከቀደመው ቀን ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛው…
በጀርመን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ርቀትን በመጠበቅ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች በሯን ክፍት አደረገች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በርሊን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ በአንድ መስጅድ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች እንዲጠቀሙ ፈቅዳለች።
ፈቃዱ የተሰጣቸው በበርሊን በሚገኘው ዳር አሳላም መስጅድ የሚፈለገውን ያህል ርቀት በመጠበቅ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን…
በፓኪስታን 99 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን 99 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ።
አውሮፕላኑ ከላሆር በመነሳት መድረሻውን ጂናህ አድርጎ በመብረር ላይ እያለ ካራቺ ከተማ አቅራቢያ መከስከሱን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የአደጋ ጊዜ…