Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ልጆች ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ልጆች ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ ማድረጋቸውን አስታወቁ። የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ወንድ ልጅ የሆነው ሳላህ ካሾጊ በትዊተር ገፁ ልጆቹ ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ ማድረጋቸውን ይፋ አድርጓል። በዚህ በተባረከው…

ቻይና የ2020 የኢኮኖሚ ዕድገት ግብን እንደማታስቀምጥ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና አመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ግብን እንደማታስቀምጥ አስታወቀች። የኮሮና ቫይረስ በኢኮኖሚ ላይ ካስከተለው ተፅእኖ ጋር በተያያዘ ቻይና ከፈረንጆቹ 1990 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አመታዊ አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ግብ እንደማይኖራት…

በህንድ ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ነፍሰጡር እናቶች ከ100 በላይ ህጻናት ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ተወልደዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በህንድ ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ነፍሰጡር እናቶች ከ100 በላይ ህጻናት ነጻ ሆነው መወለዳቸው ተሰምቷል። በምዕራብ ህንድ ሙምባይ የሚገኝ ሆስፒታል በሎክማኒያ ቲልካ ሆስፒታል ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ነፍሰጡር እናቶች 115…

በህንድና ባንግላዲሽ ከባድ አውሎ ንፋስ ባስከተለው አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012(ኤፍ ቢሲ)አምፋን ተብሎ የሚጠራው ከባድ አውሎ ንፋስ በህንድና ባንግላዲሽ ባስከተለው አደጋ ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፈ ተነገረ ፡፡ ዝናብን በቀላቀለው ከባድ አውሎ ነፋስ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች ቀያቸውን ለቀው መውጣታቸውም ነው…

በደቡብ ሱዳን  በእርስ በርስ ግጭት የ300 ሰዎች  ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት የ300 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።   በሀገሪቱ በስተምሥራቅ በጆንግሌይ ግዛት በቅርቡ በተቀሰቀሰው ግጭት ሕይወታቸው ካለፈው 300 ሰዎች መካከል ሶስት…

በዓለም ላይ በአንድ ቀን ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለማችን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በትናንትናው እለት ብቻ በዓለማችን ላይ 106 ሺህ አዲስ የኮሮና…

በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 60 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ድህነት ይጋለጣሉ – የዓለም ባንክ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ዓለም ላይ 60 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ድህነት እንደሚጋለጡ አስጠነቀቀ። የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የበርካታ ሃገራት ኢኮኖሚ ተጎድቷል። በወረርሽኙ ሳቢያ በሚሊየን…

ህንድና ባንግላዴሽ በአውሎ ነፋስ ስጋት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከመኖሪያቸው እያሸሹ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድና ባንግላዴሽ በአውሎ ነፋስ ስጋት ሳቢያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውን ከመኖሪያቸው እያሸሹ ነው። የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አምፋን የተባለውና በደረጃ 5 የተመደበው አውሎ ነፋስ በሁለቱ ሃገራት ከሰዓታት በኋላ በወጀብ የታጀበ ከባድ…

ብሪታኒያ ማሽተትና ጣዕም ማጣትን የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ አካተተች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሪታኒያ ሰዎች ራሳቸውን ችለው እንዲገለሉ ከሚያደርጉ  የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማሽተት አለመቻል ወይም ጣዕም ማጣትን ማካተቷ ተነግሯል ። እስካሁን ድረስ ሰዎች ራሳቸውን የሚያገሉት ትኩሳትና ማሳል  ምልክት ብቻ ሲኖርባቸው ሲሆን፥…

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር  በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ታውቋል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ግብረ ሀይል አባል በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ በኋላ ሪክ ማቻር ባደረጉት ምርመራ…