Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
አሜሪካ በየመን የምታቀርበውን የሰብዓዊ ድጋፍ ልታቋርጥ እንደምትችል ገለፀች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሃውቲ አማጽያን ትብብር ካላደረጉ አሜሪካ በየመን የምታቀርበውን ድጋፍ ልታቋርጥ እንደምትችል ገለፀች።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት የሀውቲ አማጽያኑ የእርዳታ ማጓጓዙን ማስተጓጎል ካላቆሙ በስተቀር ከመጋቢት ወር ጀምሮ የሰብዓዊ ድጋፉን…
የግብፅ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብፅ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በ91 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
በፈረንጆቹ 2011 በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን የተወገዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሀገሪቷን ለ30 ዓመታት መርተዋል።
የሀገሪቱ መንግስት ቴሌቪዥን እንደዘገበው…
አለም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የበለጠ መስራት አለበት-የአለም ጤና ድርጅት
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) አለም አሳሳቢነቱ በየቀኑ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል መዘጋጀት እንዳለበት የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
በወረርሽኙ በተለያዩ ሀገራት ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መጠቃታቸውን ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡
የዓለም ጤና…
ሩሲያና ቱርክ በሶሪያ ጉዳይ ተፋጠዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ጉዳይ ላይ ያላቸው ልዩነት እየሰፋ ነው።
የተለያዩ ሀገራት በሶሪያ ቀውስ የሚያደርጉት ተሳትፎ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት የሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
በሶሪያው የእርስ በርስ ጦርነት በቱርክ…
በኩዌት፣ ባህሬን እና አፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት፣ ባህሬን እና አፍጋኒስታን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።
መነሻውን ከወደ ቻይና ውሃን ግዛት ያደረገው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጭ በርካታ ሃገራትን እያዳረሰ ነው።
በዚህም በኩዌት ሶስት እንዲሁም በባህሬን እና…
ሰሜን ኮሪያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ 380 የውጭ ሃገር ዜጎችን ወደ ማቆያ ስፍራ አስገባች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመስጋት 380 የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን ወደ ማቆያ ስፍራ ማስገባቷ ተነገረ።
ወደ ማቆያ ስፍራ የተወሰዱት አብዛኛዎቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ዲፕሎማቶች ሲሆኑ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በሚገኝ ጣቢያ ውስጥ…
እስራኤል በጋዛ እና ሶሪያ በሚንቀሳቀሰው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና በሶሪያ በሚንቀሳቀሰው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።
የሃገሪቱ ጦር በደቡባዊ ደማስቆ እና ጋዛ በመሸገውና ራሱን የፍልስጤም እስላማዊ ታጣቂ ብሎ በሚጠራው ቡድን ይዞታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት…
ዶናልድ ትራምፕ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ህንድ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ህንድ ገቡ።
ፕሬዚዳንቱ ህንድ ሲደርሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ለሁለት ቀናት ጉብኝት ህንድ የገቡት ፕሬዚዳንቱ…
በቱርክ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ቱርክ ቫን ግዛት በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱሊማን ሶይሉ ፥በኢራን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ቫን ግዛት በዛሬው ዕለት የመሬት መንቀጥቀት አደጋ መከሰቱን ተናግረዋል።…
በደቡብ ኮሪያ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መነሻውን ቻይና ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ወደ ደቡብ ኮሪያ መዛመቱ ተነግሯል።
በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ነው የተገለፀው።
በደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ብቻ በእጥፍ…