Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ባሕርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 አሸንፏል። የጣና ሞገዶቹን የማሸነፊያ ግቦች ግርማ ዲሳሳ እና ቸርነት ጉግሳ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቀጥሎ በተካሄደው የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
Read More...

የሻምፒየንስ ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ 11

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳምንቱ አጋማሽ በተከናወኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ፒኤስጂ አርሰናልን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ባርሴሎና ከኢንተር ሚላን 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡ በሁለቱ ጨዋታዎች ድንቅ የነበሩ 11 ተጫዋቾች በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ይፋ ተደርገዋል፡፡ በግብ ጠባቂነት ጣሊያናዊው የፒኤስጂ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ለአውሮፓ መድረክ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲክ ቢልባኦ ከማንቼስተር ዩናይትድ እንዲሁም ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከቦዶ ግሊምት ይገናኛሉ። በውድድር ዓመቱ በፕሪሚየር ሊጉ በ15 ጨዋታዎች ተሸንፎ መጥፎ ሪከርድ የተመዘገበበት ዩናይትድ፥ በተቃራኒው በአውሮፓ መድረክ ምንም ሽንፈት ያላስተናገደ ብቸኛው ክለብ ነው።…

አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ነቢል ኑሪ ለአዳማ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

ስሑል ሽረ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መርሐ ግብር ስሑል ሽረ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሠዓት በተካሄደው ጨዋታ ፀጋዬ ብርሃኑ ለወላይታ ድቻ እንዲሁም ብርሃኑ አዳሙ ለስሑል ሽረ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡ የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል አመሻሽ 12…

የኢትዮጵያ ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር በጦር ውርወራ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛው የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር የኢትዮጵያ ፖሊስ በሴቶች የጦር ውርወራ የፍጻሜ ውድድር 1ኛ እና 2ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኗል። በውድድሩ የኬኒያ ፖሊስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። በወንዶች ጦር ወርወራ የኬኒያ ፖሊስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የኢትዮጵያ ፖሊስ 3ኛ…

አርሰናል በፒኤስጂ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ አርሰናልን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የፒኤስጂን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ ከመረብ አሳርፏል። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ምሽት በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም…