Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሊዊስ ናኒና ኑዋንኩ ካኑ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ኑዋንኩ ካኑ በኢትዮጵያ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን አሉ። ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ የገቡት የቀድሞ እግር ኳስ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ የዓመት ምስረታ በዓል ላይ እንዲገኙ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል። ፖርቹጋላዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒ÷ ኢትዮጵያ በመምጣቱ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያን…
Read More...

የሶስቱ አናብስት አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው በጥንቃቄ እንዲጫዎት አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት እሁድ በሚከናወነው የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ቡድናቸው በጥንቃቄ እንዲጨዋት አስጠንቅቀዋል፡፡ አስደናቂውን የሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ ቡድን በእለተ ሰንበት የሚገጥሙት የ53 ዓመቱ አሰልጣኝ÷ ቡድናቸው ስፔንን በማሸነፍ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫን ወደእጃቸው…

የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክን አስመልክቶ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክን አስመልክቶ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና የሽኝት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው። በመርሃ ግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣የቱሪዝም…

የካፍ ክለቦች ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024/25 የውድድር ዘመን የካፍ ክለቦች ውድድር የምድብ ድልደል ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዩጋንዳው ቪላ ጋር ሲመደብ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ ክለብ ጋር ተመድበዋል፡፡

የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡ ፌደሬሽኑ ከዚህ በፊት የ2017 የውድድር ዘመን የዝውውር ጊዜ ሐምሌ 15 ቀን 2016 እንደሚከፈት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቀኑን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዲሱ…

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኦሊቪየ ዢሩ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቪየ ዢሩ በ37 ዓመቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡ ዢሩ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ምሽት ሀገሩ ፈረንሳይ ከስፔን ጋር ጨዋታዋን ስታደርግ ተቀይሮ በመግባት የተጫወተ ሲሆን በሽንፈት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ በይፋ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አግልሏል፡፡…

ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ይለያል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን የሚለይበት የእንግሊዝና ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ሁለተኛ መርሐ-ግብር እንግሊዝ ከኔዘርላንድስ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም የሚያደርጉት ብርቱ ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡ በሩብ ፍጻሜው እንግሊዝ…