ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሃምበሪቾን 6 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሃምበሪቾን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል።
የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች መሐመድ ኑር ናስር (2)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ፍ)፣ አማኑኤል አድማሱ፣ ጫላ ተሺታና የሃምበሪቾ ግብ ጠባቂ ምንታምር መለሰ (በራሱ ግብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
የሃምበሪቾን ብቸኛ ግብ ደግሞ አላዛር አድማሱ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና 44 ነጥብ በመሰብሰብ ከነበረበት 5ኛ ደረጃ ወደ 4ኛ ከፍ ማለት ችሏል፡፡
Read More...
በዩጂን ዳይመንድ ሊግ ድርቤ ወልተጂ እና ጽጌ ገብረሰላማ በተለያዩ እርቀቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩጂን ዳይመንድ ሊግ ድርቤ ወልተጂ በ 1 ሺህ 500 እና ጽጌ ገብረሰላማ በ5 ሺህ ሜትር ቀዳሚ በመሆን አሸነፉ።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች አትሌት ድርቤ ወልተጂ 3 ደቂቃ 53 ሴኮንድ ከ75 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡
በሌላ ርቀት የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ጎልቶ በታየበት 5 ሺህ…
ዛሬ በተከናወኑ የሊጉ ጨዋታዎች መሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተከናወኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 1ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ…
ማንቼስተር ዩናይትድ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ በማሸነፍ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ፡፡
በዌምብሌይ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሠዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቀያይ ሰይጣኖቹ ውኃ ሰማያዊዎቹን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡
የዩናይትድን ጎሎች ግራናቾ እና ማይኖ ሲያስቆጥሩ የሲቲን ደግሞ…
የማንቼስተር ከተማ ክለቦች የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒየን ማንቼስተር ሲቲ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ዛሬ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ ይፋለማል፡፡
ጨዋታው ለንደን በሚገኘው ዌምብሌይ ስታዲየም 11 ሠዓት ላይ ይካሄዳል፡፡
በኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ታሪክ ቀያይ ሰይጣኖቹ 12 ጊዜ እንዲሁም ውኃ ሰማያዊዮቹ 7 ጊዜ ሻምፒየን ሆነዋል፡፡
ዛሬ የተከናወኑ የሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተከናወኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ የተካሄደው የባህርዳር ከተማና እና የወላይታ ድቻ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
…
ሃንሲ ፍሊክ የባርሴሎና አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ የባርሴሎና አሰልጣኝ ለመሆን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገለፀ፡፡
የ59 ዓመቱ አሰልጣኝ ከሰዓታት በፊት የተባረረውን ዣቢ በመተካት ነው የካታሎኖን ክለብ ለመረከብ የተስማሙት፡፡
ፍሊክ በሁለት ዓመት ኮንትራት ክለቡን በአሰልጣኝነት ለመረከብ መስማማታቸው የተገለፀ ሲሆን÷ አሰልጣኙ ሁለት…