ስፓርት
ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡
የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 8ኛው የዞን 3 አፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና በማስተርስ ዋና ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በዞን 3 የአፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር በታዳጊ ወጣቶችና በማስተርስ ዋና ውድድር ተሳትፋ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና በ100 ሜትር ደረት ቀዘፋ በአትሌት እስከዳር አቻምየለህ አማካኝነት…
Read More...
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት በጂግጂጋ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጂግጂጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡
በወንዶች በተደረገው የሩጫ ውድድር ከጅግጅጋ አትሌቲክስ ፕሮጀክት የተወከለው አትሌት አሕመድ መሐመድ 1ኛ፣ ከጅግጅጋ አትሌቲክስ ፕሮጀክት የተወከሉት አትሌት በረከት መሐመድ 2ኛ እንዲሁም…
ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለቦች ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ላይ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ 100 እና 75 ሺህ እንዲቀጡ መወሰኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በ6ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ከዳኞች እና…
በፕሪሚየር ሊጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
9 ሰዓት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የአዳማ ከተማ ግቦችን ሀቢብ መሐመድ እና ቢንያም አይተን ሲያስቆጥሩ÷አንተነህ ተፈራ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ጎል…
ሊቨርፑልና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳቸው የተጫወቱት ሊቨርፑልና ቼልሲ ድል ቀናቸው።
ብራይተንን ያስተናገደው ቼልሲ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በተመሳሳይ በሜዳው የተጫወተው ሊቨርፑል ፉልሃምን አስተናግዶ 4 ለ 3 አሸንፏል።
በርንማውዝ አስቶቪላን አስተናግዶ 2 ለ2 ሲለያይ፤…
በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶቹ አትሌት ሲሳይ ለማ ርቀቱን 2 ሰአት ከ1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡…
አርሰናል ዎልቭስን በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ዎልቭስን 2 ለ 1 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡
ምሽት 12፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ኦዲጋርድ የአርሰናልን ጎሎች ሲያስቆትሩ ማቲያስ ኩና የዎልቭስን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተክትሎም በውድድሩ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ…