ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ቶትንሃም ተሸንፏል፡፡
በሜዳው በርንሌን ያስተናገደው አርሰናል ትሮሳርድ፣ ሳሊባ እና ዚንቼንኮ ባስቆጠሯቸው ግቦች 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ በኦልድ ትራፎርድ ሉተን ታዎንን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ሊንደሎፍ ነው ያስቆጠረው ፡፡…
Read More...
የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ በሚደረጉ ስድስት ጨዋታዎች ጅማሮውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ዘንድሮ በሁለት ምድቦች 28 ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው ውድድሩ በሐዋሳ እና አዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከውድድሩ ቀደም ብሎም በሁለቱም ምድቦች የውድድር አመራሮች እና ተሳታፊ ክለቦች…
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላለበት ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከሴራሊዮን እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ የሚያሰልፏቸውን 23 ተጫዋቾች መለየታቸውንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ህዳር ወር መጀመሪያ…
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ሊግ እና የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህ ድልድል በምድብ ሀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀምበሪቾ ዱራሜ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወላይታ ድቻ ከደሴ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከሃላባ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ፣ ነገሌ አርሲ ከስልጤ…
አል ኢቲሃድ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተሳታፊው አል ኢቲሃድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናብቷል፡፡
የቀድሞ የቶተንሃም ሆትስፐር እና ወልቭስ አሰልጣኝ የነበሩት ሳንቶስ በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ባሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ ነው ከአሰልጣኝነት የተሰናበቱት፡፡
አሰልጣኙ ከተካሄዱ 12 ጨዋታዎች በ6ቱ ብቻ ያሸነፉ…
የዋልያዎቹ ሁለት ተጫዋቾች ከስብስቡ ውጭ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ትናንት ዝግጅት መጀመሩ ይታወሳል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር።
ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ከስብስቡ ውጭ መሆኑ ሲረጋገጥ ሌሎቹ…
የአፍሪካ ህብረት በኒው ዮርክ ማራቶን አፍሪካን ላስጠሩ አትሌቶች ምስጋና አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤት በኒው ዮርክ ማራቶን የአፍሪካን አህጉር ላስጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን አትሌቶች ምስጋና አቅርቧል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በኒው ዮርክ ማራቶን ላሸነፉ የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ…