ስፓርት
አትሌት ታምራት ቶላ ለችግረኛ ተማሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው ላሉ ችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መግዣና ለታዳጊዎች ስፖርት ማጠናከሪያ የሚሆን የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡
አትሌቱ ዛሬ በትውልድ አካባቢው ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሌልቱ ወረዳ ሚአዋ ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በዚህ ወቅትም ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መግዣና ለታዳጊዎች ስፖርት ማጠናከሪያ የሚሆን የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡
በቀጣይም አንድ ትምህርት ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ቃል የገባ ሲሆን÷ በሚአዋ…
Read More...
ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለም
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024/25 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በኬንያው ኬንያ ፖሊስ በድምር ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
ሁለቱ ክለቦች ዛሬ አበበ በቂላ ስታዲየም ባደረጉት የመልስ ጨዋታ ኬንያ ፖሊስ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ኬንያ ፖሊስ በአጠቃላይ ውጤት 1 ለ 0 በማሸነፍ…
አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው አቀበባል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በዛሬው ዕለት በትውልድ አካባቢው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሌልቱ ወረዳ ሚአዋ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።
አትሌቱ በከተማው ሲደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የወረዳው አመራሮችና የአትሌቱ ቤተሰቦች የጀግና አቀባበል አድርገውለታል።
አትሌት…
የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ እንዲሁም ሊቨርፑል ከብረንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ሲደረግ ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል እና ነጥብ ይዞ ለመውጣት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡…
መድፈኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ድላቸውን አስመዘገቡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አስቶንቪላን በሜዳው 2 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን ሁለተኛ ድል አስመዝግቧል፡፡
ጎሎቹንም ትሮሳርድ በ67ኛው እንዲሁም ፓርቴ በ77ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በቅድመ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት የተሰጠው አርሰናል ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት ብልጫ ወስዷል፡፡
በመጀመሪያው ሣምንት…
ቶተንሃም፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም፣ ማንቼስተር ሲቲና ዌስትሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሣምንት ጨዋታዎች ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዌስትሃም፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም እና ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም መሠረት÷ ቶተንሃም ኤቨርተንን 4 ለ 0፣ ዌስትሃም ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ሳውዝ ሃምተንን 1 ለ 0፣ ፉልሃም ሌስተር ሲቲን 2 ለ 1…
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዑጋንዳውን ኤስ ሲ ቪላ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከዑጋንዳው ክለብ ኤስ ሲ ቪላ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አንድ አቻ አጠናቅቋል።
ጎሎቹን ሱሌይማን ሀሚድ በ64ኛው ደቂቃ ለንድ ባንክ እንዲሁም ለኤስ ሲ ቪላ ፓትሪክ ካካንዴ በ74ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡…