Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ በሴካፋ ከ18 ዓመት የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበራት(ሴካፋ) ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛንዚባር አቻውን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በቻማዚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ እሙሽ ዳንኤል በ45ኛ፣ በ55ኛ እና በ56ኛ ደቂቃ ላይ ሶስት ግቦችን አስቆጥራ ሃትሪክ ሰርታለች። ማህሌት ምትኩ ደግሞ በ6ኛ እና በ23ኛ ደቂቃ ላይ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር፤ ትንቢት ሳሙኤል ደግሞ በ44ኛ ደቂቃ ላይ…
Read More...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገብቷል፡፡ ዋልያዎቹ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያረፉ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት ቀናት ልምምድ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው ሐምሌ 26 በዋሽንግተን ዲሲ ከጋያና ብሔራዊ ቡድን እናሐምሌ 29 በሳውዘርን ክረሰንት ስታዲየም ከአትላንታ ሮቨርስ…

ቢኒያም በላይ እና ዮሴፍ ታረቀኝ የውድድር አመቱ ኮከቦች በመሆን ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች ቢኒያም በላይ የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመረጠ። ‘የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፎትቦለርስ አሶሴሽን’ እንዳስታወቀው ተጫዋቹ፥ በየክለብ አምበሎች በተደረገ ምርጫ ቀዳሚ በመሆን የውድድር አመቱ ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ቢኒያም በላይ በዚህ የውድድር አመት ክለቡ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአዲዳስ ኩባንያ ጋር ትልቁን የመለያ ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ ጋር ለቀጣይ 10 ዓመታት ተጨማሪ ውል መፈራረሙን አስታወቀ። በውሉ መሰረትም ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር ያላው የውል ሥምምነት እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 2035 ድረስ ይቆያል ነው የተባለው፡፡ በዚህም…

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ። ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም ጋር የተደለደሉት ፈረሰኞቹ ÷ ነገ ቢሾፍቱ በሚገኘው ክብር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ታውቋል። ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነሐሴ 12 ወይም 13/2015 ዓ.ም…

ኢትዮጵያ ቡሩንዲን 2 ለ 0 ረታች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋ ቡሩንዲን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ እሙሽ ዳንኤል በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ጎሎች ነው ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋን የረታችው፡፡ የሴካፋ ሴቶች ከ 18 ዓመት በታች ውድድር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ…

የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ። ክብረ ወሰኑን በደቡብ አሜሪካ ከ20 አመት በታች የአትሌቲካስ ሻምፒዮና ላይ፥ የሱሪናሙ አትሌት ኢሳማዴ አሲንጋ 9 ሰከንድ ከ89 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሻሽሎታል። የብራዚሉ ኤሪክ ካርዶሶ እና የኮሎምቢያው…