ስፓርት
የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ (ቴሌቶን) ዛሬ ከምሽቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
መቻል ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ የመመለስና ክለቡን የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ሲሆን÷ የገቢ ማሰባሰቢያውም የእዚሁ ሥራ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ክለቡን ለማጠናከር እና በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ሕብረተሰቡ፣ ባለሃብቶች፣ ተቋማት እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡…
Read More...
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች 3 ዋንጫዎችን በማንሣት የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በሦስት ዘርፎች የተካሄዱ ውድድሮችን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡
በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ለአራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የክለቦች የቦክስ ውድድር ተጠናቅቋል፡፡
በውድድሩ ሰባት ክለቦች የተካፈሉ ሲሆን÷ የሴቶቹ ውድድር በ “ኤ” ምድብ እንዲሁም የወንዶቹ…
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የዋንጫውን አሸናፊ የለዩ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ቀን 9 ሰዓት ላይ ተካሂደዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት…
የፈረንሳይ ከዋክብት የጎል ድርቅ በአውሮፓ ዋንጫ አዲስ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የላቀ ክህሎት ያላቸው ከዋክብትን የያዘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በክፍት ጨዋታ አንድም ግብ ሳያስቆጥር ግማሽ ፍጻሜን በመቀላቀል አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡
ትናንት ምሽት ከ120 ደቂቃ ፍልሚያ በኋላ ፈረንሳይ ፖርቹጋልን በመለያ ምት 5 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፏ ይታወሳል።
የትናንት…
በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ ከስዊዘርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር እንግሊዝና ስዊዘርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
በዚህም መሰረት እንግሊዝ ከስዊዘርላንድ ምሽት 1:00 ላይ በዱሴልዶርፍ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በጥሎ…
ወልቂጤ ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ወልቂጤ ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9:00 ላይ በተካሄደ የሊጉ ጨዋታ አዳነ በላይነህ ባስቆጠራት ግብ ወልቂጤ ከተማ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በፓሪስ ኦሊምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ውድድሮች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በዚህም ፡-
800 ሜትር ሴቶች አትሌት ፅጌ ድጉማ፣አትሌት ሐብታም ዓለሙ፣አትሌት ወርቅነሽ መለሰ፣አትሌት ንግስት ጌታቸው (ተጠባባቂ)
1ሺህ…