ስፓርት
ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር በሀጎስ ገብረህይወት አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።
አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት 13:38.12 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት አሸንፏል።
Read More...
ኢትዮጵያ በሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ52 እና በ66 ኪሎ ግራም ሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።
ቤተልሔም ገዛኸኝ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው በፍጻሜ ውድድሩ የሞሮኮዋን ቼዳል ራባብ 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊቷ ቦክሰኛ…
አትሌት ዘውዲቱ አደራው በሴቶች ግማሽ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አስገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዘውዲቱ አደራው 2ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡
አሁን ላይ የወንዶቹ የ20 ኪሎ ሜትር ውድድር እየተካሄደ ሲሆን÷ አትሌት ተሰማ መኮነን፣ማስረሻ ብሪ እና ሃፍታሙ አባዲ ኢትዮጵያን ወክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ብርና ነሐስ አስመዘገበች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ብርና ነሐስ አስመዝግበዋል፡፡
በውድድሩ ውዴ ከፋለ ሁለተኛ የወጣች ሲሆን ፥ ተካን አማረ ሦስተኛ በመውጣት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በወንዶች የምርኩዝ ዝላይ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በወንዶች የምርኩዝ ዝላይ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡
ፌዴሬሽኑ እንዳለው ፥ የነሐስ ሜዳሊያውን ያገኘው አትሌት አበራ ለማ ሲሆን ፥ አራት ሜትር በመዝለል የነሐስ ሜዳልያውን እንዳጠለቀ ተገልጿል፡፡
ካፍ የአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት ላይ እንዲከናወኑ ያስቀመጣቸው ሥራዎች ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት መመዘኛ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ እንዲከናወኑ ያስቀመጣቸው ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።
በሚኒስቴሩ የስፖርት ፋሲሊቲ ልማትና አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አስማረ ግዛው÷ ካፍ ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረት…
በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የመሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ሎሚ ሙለታ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
አትሌቷ 9 ደቂቃ 26 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው 3ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው፡፡
እንዲሁም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡…