ስፓርት
ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ቀን 10 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በዚህም የፋሲል ከነማን ጎሎች ቃልኪዳን ዘላለም እና አምሳሉ ጥላሁን ሲያስቆጥሩ የሲዳማ ቡናን ጎሎች ደግሞ ይክል ኪፕሩል አስቆጥሯል፡፡
Read More...
አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡
አትሌት ጀማል ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በመግባት ሲሆን÷ ይህም የግሉ ፈጣን ሠዓት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚሁ መሠረት 10:00 ሠዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
እንዲሁም 1:00 ሠዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን እንደሚደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡
ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት 21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩም ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ እና መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
መነሻ እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አካባቢ ያደረገው የሩጫ ውድድር÷ “የሴቶችን አቅም…
በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላሬዶ ከተማ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡
አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡
የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።
በመጪው ሐምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መነሻ በማድረግ የተጀመረው ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአፋር ክልሎች…
በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ጋና ገባ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው ከ90 በላይ ሰዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ጋና አክራ ገብተዋል።
ልዑኩ ከአጭር እስከ መካከለኛ ርቀት የሚወዳደሩ አትሌቶች እና የሴቶች የቅርጫት ኳስ ቡድንን ያካተተ ነው፡፡
በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱም በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬን…