ስፓርት
የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ ጨዋታዎች በሐዋሳ እንደሚካሄዱ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ27 እስከ 30ኛ ሣምንት ያሉ ጨዋታዎች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዳቸው እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማኅበር እንዳስታወቀው÷ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ መልስ የፕሪሚየር ሊጉ የ27ኛ ሣምንት ጨዋታዎች ሐሙስ ሰኔ 6 ቀን 2016 ይጀምራሉ፡፡
ከ27ኛ ሣምንት ጀምሮ እስከ 30ኛ ሣምንት ያሉ ጨዋታዎችም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ ማኅበሩ አረጋግጧል፡፡
Read More...
ኤንዞ ማሬስካ የቼልሲ አሰልጣኝ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ44 ዓመቱ ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቼልሲን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት በይፋ ፊርማውን አስቀምጧል፡፡
ተሰናባቹን አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ተክቶ እስከ ፈረንጆቹ 2029 የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ለማሰልጠን ለፈረመው ማሬስካ ዝውውር ቸልሲ 10 ሚሊየን ዩሮ እንደሚከፍል ተገልጿል፡፡
ከዝውውሩ ጋር የተያያዙ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቢሳው አቀና
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ መዲናዋ ቢሳው ተጉዟል።
23 ተጫዋቾችን ያካተተው ልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ በቶጎ (ሎሜ) አድርጎ ቢሳው ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ…
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ የዓመቱን የዓለም ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ለሜቻ ግርማ የዓመቱን የዓለም ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ፡፡
በዚህም መሠረት በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል የወንዶች ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ 8 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ÷ ሳሙኤል…
በማድሪድ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ጥሩነሽ ዲባባ 3ኛ ስትወጣ ዳዊት ወልዴ በቀደሚነት አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ማድሪድ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር በሴቶች አንጋፋዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በወንዶች ደግሞ ዳዊት ወልዴ በቀዳሚነት አጠናቋል፡፡
ጥሩነሽ 10 ኪሎ ሜትሩን በ30 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ በመጨረስ ነው 3ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው፡፡
በወንዶች የ10 ኪሎ ሜትር…
የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍጻሜ ጨዋታ ነገ ምሽት በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023/24 አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ነገ ምሽት በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊደረግ ቀጠሮ በተያዘለት ታላቁ የፍጻሜ ጨዋታ የአውሮፓ ሻምፒዮንሰ ሊግ ንጉሶቹ ሪያል ማድሪድ እና የጀርመኑ ክለብ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የባለ ትልቁ ጆሮ ዋንጫ ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡
በጨዋታው ሎስ…
ሐጎስ ገብረህይወት በ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐጎስ ገብረህይወት በዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር አሸንፏል፡፡
በውድድሩ 12፡36፡73 ሰዓት በመግባት ሲያሸንፍ ፥ በ5ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ሪከርድ ለመስበር በሁለት ሰከንድ ዘግይቶ መግባቱ ተገልጿል፡፡
አትሌቱ በተሳተፈበት በዚህ ውድድርም በታሪክ የምንጊዜም ሁለተኛውን ፈጣን…