ስፓርት
ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ከማላዊ አቻው ጋር እያካሄደ ነው፡፡
ጨዋታው በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በምድብ 4 የማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ያለችው ኢትዮጵያ÷ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ በሦስት ነጥብ በምድቡ የመጨረሻው አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…
Read More...
ቼልሲ ንኩንኩን ሲያስፈርም አርሰናል ለራይስ 90 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቧል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በቀጣዩ ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር በስፋት እየተሳተፉ ነው።
በተለይም የዝውውር መስኮቱ የተከፈተላቸው የእንግሊዝ ክለቦች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲሆን÷ በዚህም ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩን ከአር ቢ ሌፕዚግ አስፈርሟል።
ንኩንኩ ክለቡን ለተረከቡት አሰልጣኝ…
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣዩ ዓመት ፋሲል ከነማን ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡
በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ የጀመረው ፋሲል ከነማ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለ ሲሆን÷ በ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ ክለቡ በዘንድሮው…
ለ34 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ከቻድ ጋር ለተደለደለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 34 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ፡፡
ቡድኑ ለጨዋታው ለሚያደርገው ዝግጅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለተጫዋቾቹ ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ሰኔ 13 ቀን…
የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36 ክለቦች በ71 ምድብ እና በአምስት የውደድር ዘርፍ በሁለቱም ፆታ የሚሳተፉበት የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌደሬሽን የበላይ ጠባቂ ማስተር ወጋየሁ በኃይሉ በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶን ለማሳደግ የክለቦች…
“ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር አይኖርም” – ፊፋ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር እንደማይኖር ገለጸ፡፡
በብራዚላዊው አጥቂ ቪኒሺየስ ጁኒየር የሚመራ ከተጫዋቾች የተውጣጣ የፀረ- ዘረኝነት ኮሚቴ ማቋቋሙን ፊፋ ይፋ አድርጓል፡፡
የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያንኒ ኢንፋንቲኖ ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር…
በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የአንድ ማይል ውድድር ብርቄ ሃየሎም የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኖርዌይ ኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የአንድ ማይል ውድድር ብርቄ ሃየሎም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች፡፡
አትሌት ብርቄ ርቀቱን በ4 ደቂቃ 17 ሰከንድ 13 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ክብረወሰን በመስበር ያሸነፈችው፡፡
በውድድሩ ወርቅነሽ መለሰ 5ኛ ፣ ሂሩት…