Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሃላንድ የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን ሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጫዋች ኧርሊንግ ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። የ22 አመቱ ኖርዌያዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ክለቡ ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ በሊጉ 35ኛ ጎሉን አስቆጥሯል። ይህም ከዚህ ቀደም በቀድሞወቹ እንግሊዛውያን አጥቂዎች አንዲ ኮል እና አለን ሽረር በአንድ የውድድር አመት የተመዘገበውን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን እንዲሰብር አስችሎታል። ሁለቱ አጥቂዎች በ34 ጎሎች በአንድ የውድድር…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ 9፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቻል ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ከነዓን ማርክነህ እና እስራኤል እሸቱ የመቻልን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥሩ÷ ብቸኛዋን ድሬዳዋ ጎል ሙኸዲን ሙሳ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን…

ከ20 ዓመት በታች በ5ሺህ ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመውጣት ድል አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ ንዶላ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ማጠቃለያ ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመውጣት ድል አድርገዋል፡፡ አትሌት ውብርስት አስቻለ ቀዳሚ በመሆን ለሀገሯ ወርቅ ስታስገኝ፣ አይናዲስ መብራቴ 2ኛ በውጣት ብር እንዲሁም   አስማረች አንለይ 3ኛ በውጣት ነሃስ አስገኝተዋል፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያ 7 የወርቅ…

የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ ንዶላ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ በሻምፒዮናው መዝጊያ ዕለት የቡድን 5 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡ አሁን ላይ ከ18 አመት በታች የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የእርምጃ ውድድር  አበቡ አያሌው ሁለተኛ…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ መሐመድ ኑር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር÷…

ሻሸመኔ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሻሸመኔ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማን ሽንፈት ተከትሎ ከ15 የውድድር ዘመናት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ ሻሸመኔ ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ በሀገሪቱ ትልቁ ሊግ ተሳትፎ ያደረገው በ2000 ሚድሮክ ሚሌኒየም ፕሪሚየር ሊግ ላይ ነበር።

የእርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ ለሀገሩ ወርቅ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ምስጋና ዋቁማ ወርቅ አገኘች፡፡ አትሌት ምስጋና ዋቁማ በ10 ሺህ ሜትር የእርምጃ ውድድር አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ነው ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው፡፡ በዛምቢያ ንዶላ የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና…