ስፓርት
ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
የዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ማርከስ ራሽፎርድ እና ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል፡፡
ሁለቱም የፍፁም ቅጣት ምቶች በአርጀንቲናዊው የመስመር አጥቂ ጋርናቾ የተገኙ ሲሆን÷ በውድድር ዓመቱም ለክለቡ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ያስገኘ ብቸኛ ተጫዋች ሆኗል፡፡
የ28ኛ ሣምንት መርሐ-ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 2፡30 የዋንጫ ተፎካካሪው አርሰናል በሜዳው ብረንት ፎርድን…
Read More...
13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በጋና አክራ በይፋ ተከፍቷል፡፡
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ÷ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነሮች፣ የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፋ ዶን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
ውድድሩን…
የሜሲን ስም በመጥራት ከሃማስ እገታ የተረፉት የ90 ዓመት አዛውንት
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ90 ዓመቷ አዛውንት የሊዮኔል ሜሲን ስም በመጥራት ከሃማስ እገታ መትረፋቸው መሰማቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት በፈፀመበት በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዕለት ነገሩ የተፈጸመው።
በዕድሜ የገፉት የ90 ዓመቷ አዛውንት ኤስተር ኩኒዮ ቤታቸው ውስጥ ከተቀመጡበት የሃማስ አጋቾች በድንገት ይገቡና…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ትዕግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ይሳተፋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና የወቅቱ የሴቶች ማራቶን ክበረ ወሰን ባለቤት ትዕግስት አሰፋ በ2024 የለንደን ማራቶን ውድድር እንደሚሳተፉ የለንደን ማራቶን አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
የ41 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በ2023ቱ የቫሌንሲያ ማራቶን 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በመግባት በአንጋፋ ዕድሜ ዘርፍ አዲስ ክብረወሰን…
በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ።
የባህልና የስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ…
በግላስጎ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች።
19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በፈረንጆቹ ከመጋቢት 1 እስከ 3 ቀን በስኮትላንዷ መዲና ግላስጎ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን÷ በሻምፒዮናው ከ130 በላይ ሀገራት የተወጣጡ ከ650 በላይ…
ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎው በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።
በሻምፒዮናው በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ፍሬወይኒ ሀይሉ 4:01.46 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።
በተመሳሳይ በሻምፒዮናው የሴቶች 800 ሜትር…