Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዋንጫ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን የሚያሳትፈው የድሬ ዋንጫ ከየካቲት 16 ጀምሮ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይደረጋል። በውድድሩ ለሚሳተፉና ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም ከየካቲት 13 ጀምሮ በተዘጋጀላቸው ሆቴል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። ቡድኑ በአመዛኙ በአዳዲስ ተጫዋቾች መዋቀሩን የእግኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
Read More...

የሀሪ ኬን የዋንጫ እርግማን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቶተንሃም እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪው ሃሪ ኬን ከአዲሱ ትውልድ ምርጥ አጥቂዎች ውስጥ ስሙ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ቢያደርግም ዋንጫ አንስቶ በመሳም ረገድ ግን ዕድል ከእሱ ጋር አይደለችም። የ30 ዓመቱ አጥቂ በክለብ እና በብሄራዊ ቡድን ባደረጋቸው…

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ሊቨርፑል ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 4 ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡ በሌላ በኩል አርሰናል በርንሌይን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ÷ወልቭስ ደግሞ ቶተንሃምን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ…

በጋምቤላ ክልል አቀፍ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በጋምቤላ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። ውድድሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት÷ ስፖርት የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ ስላለው ውድድሩን በጨዋነት ማካሄድ ይገባል። በመሆኑም ውድድሩ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ፍፃሜውን እንዲያገኝ…

2ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ከ16ኛ ሳምንት ጀምሮ…

ዮሴፍ ገብረወልድ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሟል፡፡ ቡድኑ በጋና አስተናጋጅነት በሚካሄው የአፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ ተሳታፊ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ከየካቲት 29 ቀን ጀምሮ ለሚካሄው ውድድርም ቡድኑን እንዲያዘጋጅ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር…

የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኑ የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ እውቅናና ሽልማት ተብርክቶለታል፡፡ ዝሆኖቹ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በአቢጃን ጎዳናዎች ላይ የአፍሪካን ዋንጫ በመያዝ ለብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች እና ለሀገሪቱ  ዜጎች የክብር ዋንጫውን በተለያዩ የትርዒት ሰልፎች አሳይተዋል፡፡ ከሻምፒዮኖቹ…