ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል።
ዛሬ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የተጫወተው አዳማ ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለአዳማ ከተማ ቢኒያም አይተን ዊሊያም ሰለሞን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
Read More...
የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በቦነስ አይረስ የጀግና አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በዋና ከተማዋ ቦነስ አይረስ የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
አርጀንቲና ከትናንት በስቲያ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ፈረንሳይን በመለያ ምት አሸንፋ ባለ ድል መሆኗ ይታወሳል።
የአርጀንቲና የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ዛሬ ንጋት ላይ ቦነስ አይረስ ሲደርስ፥ ብዙ ህዝብ…
ካሪም ቤንዜማ ከብሄራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ከብሄራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል፡፡
የ2022 ባሎን ደ ኦር አሸናፊው ካሪም ቤንዜማ በአሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻምፕ ስብስብ ውስጥ ቢካተትም በዓለም ዋንጫው ጅማሮ ባጋጠመው ጉዳት ከውድድሩ ውጭ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ተጫዋቹ በትዊትር ገፁ ባሰፈረው መልዕክትም፥ በግሉ ለደረሰበት ስኬት…
በፕሪሚየር ሊጉ መቻል ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ባህርዳር ከነማን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ መቻል ከመመራት ተነስቶ በሃሉ ግርማ፣ በረከት ደስታ እና ከነዓን ማርክነህ ባስቆጠሯቸው ግቦችአሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ የጣና ሞገዶቹ ፕሪሚየር ሊጉን የሚመሩበትን…
በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈረንሳይ ደጋፊዎችን በማስደሰታችሁ ኮርተንባችኋል – ኢማኑኤል ማክሩን ለብሄራዊ ቡድናቸው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈረንሳይ ደጋፊዎችን በማስደሰታችሁ ኮርተንባችኋል ሲሉ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በፍፃሜ ጨዋታው በአርጅንቲና በመለያ ምት ተሸንፎ ዋንጫውን ያጣውን ብሄራዊ ቡድናቸውን መልበሻ ክፍል ድረስ በመሄድ አፅናንተዋል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያዎች…
የፕሪሚየር ሊጉ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።
በዓለም ዋንጫው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት እንደሚጀመርም ተገልጿል።
ባህር ዳር ከተማ ከመቻል ከቀኑ 10 ሰአት እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና ከምሽቱ…
አርጀንቲና የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምት በማሸነፍ የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሉሳይል አይኮኒክ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በዚህም ፈረንሳይ እና አርጀንቲና መደበኛ ጨዋታውን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን÷…