ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
በዚህም 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግብ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ አስቆጥሯል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 1ለ 0 አሸንፏል፡፡
አቤል ከበደ የማሸነፊያ ግቧን…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ደስታ ዮሐንስ በ72ኛው እና ጀሚል ያዕቆብ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ27 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ሲል…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለና አልማዝ አያና የሚሳተፉበት የለንደን ማራቶን የፊታችን እሑድ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላላቅ አትሌቶች የሚፋለሙበት የ2023 የለንደን ማራቶን የፊታችን እሑድ ሚያዚያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
በውድድሩ በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ የሚካፈል ሲሆን÷ ለአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ 2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመሮጥ ሁለተኛው…
በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂደዋል፡፡
በዚህም ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ባደረጉት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ተቀይሮ የገባው የአማካይ ተጫዋች መለሰ ሚሻሞ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሀዲያ…
አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና 1 አቻ ተለያዩ፡፡
ጎሎቹን ተመስገን ደረሰ ለአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ሞሀመድ ናስር ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥረዋል፡፡
ክለቦቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ በነበሩበት 12ኛ እና 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በሌላ የጨዋታ…
ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሊቨርፑል ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡፡
ማኔ የቡድን አጋሩን ሌሮይ ሳኔ በመልበሻ ክፍል ውስጥ በቡጢ በመደብደቡ ነው የገንዘብ ቅጣቱ የተላለፈበት፡፡
የተጣለው የገንዘብ ቅጣትም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡…
በቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡
አማኔ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 50 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ሁለተኛ ደረጃን መያዝ የቻለችው፡፡
ርቀቱን ኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦብሪ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት አጠናቅቃለች፡፡…