ስፓርት
በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡
በወንዶቹ ምድብ አብዲሳ ቶላ በ2:05:42 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ÷ደሬሳ ገለቴና ሃይማኖት አለው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በወንዶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊያኑ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ የ2023ቱን የዱባይ ማራቶን በበላይነት አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በሴቶቹ የዱባይ ማራቶን ውድድር ደራ ዲዳ ርቀቱን…
Read More...
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፖላንድ የአንድ ማይል ውድድር ሁለተኛውን ፈጣን ሰአት አስመዘገበች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ትናንት ምሽት በፖላንድ ቶረን በተካሄደ የቤት ውስጥ የአንድ ማይል ውድድር የዓለማችን ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡
አትሌቷ ርቀቱን 4 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ስታጠናቅቅ ይህ ሰዓትም ከገንዘቤ ዲባባ በመቀጠል ሁለተኛው የዓለማችን ፈጣን ሰዓት ሆኖ…
ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በመጪው ቅዳሜ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በሚያደርጉት የሸገር…
የ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች የተሳተፉበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ በሁለቱም ጾታ በ218 ነጥብ 1ኛ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡
እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ…
ተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዘመ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዝሟል ።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት በ12ኛ ሳምንት የሊጉ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ለጊዜው ባልተገለፀ ምክንያት…
በፕሪሚየር ሊጉ ከዕረፍት መልስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ተሳትፎ እና ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ ከ40 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ…