ስፓርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ፡፡
በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር መግለጹ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጅ ውድድሩ የሚጀመርበት ቀን ቀድሞ ከተገለፀው በአንድ ሣምንት መራዘሙን ከማኅበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ቀን ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረትም ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የ12ኛ ሳምንቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም…
ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡
ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ለ46 አትሌቶቹ የተለያዩ ማዕረጎችን ሰጥቷል፡፡
በዚህም በኦሪገን ማራቶን ሻምፒዮን የነበረው አትሌት ታምራት ቶላ የዋና ሳጅን ማዕረግ የነበረው ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ…
የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን በዛሬው እለት ከሊቢያ አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አስመልክተው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አማካዩ ጋቶች ፓኖም መግለጫ ሰጥተዋል፡፡…
የዕለተ ሰኞ የውጭ አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች
ሞሮኮ ከቻን ውድድር ራሷን ማግለሏ ተሰምቷል፤ይህን ተከትሎም በቻን የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ከሞሮኮ ጋር ጨዋታ የነበራት ሱዳን በፎርፌ አሸንፋለች፡፡
የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን ሲል ፈረንሳዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ተከላካይ ራፋይል ቫራን ተናግሯል፡፡
ቫራን ይህን ያለው በማንቹሪያ ደርቢ ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር…
በሂውስተን ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በተካሄደው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጸታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በሂውስተን የወንዶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ አሸንፏል፡፡
አትሌት ልዑል ርቀቱን 1፡00፡34 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈው፡፡
በሴቶች ግማሽ ማራቶን ምድብ ደግሞ አትሌት…
በስፔን በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው አሸነፈች፡፡
ውድድሩን 29 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በመግባት ነው አትሌት የዓለምዘርፍ ያሸነፈችው፡፡