Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የወንዶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡ ውድድሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ በወጣው መርሐ ግብር መሰረት ፥ በምድብ አንድ፥ ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ፣ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በምድብ ሁለት ኡጋንዳ ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ቡርንዲ መመደባቸውን የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን…
Read More...

ፌዴሬሽኑ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ውል አራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውላቸውን ለማራዘም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል። አሰልጣኙ ውላቸው መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ÷ይህን ተከትሎም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ስምምነት መፈፀሙ ታውቋል፡፡ አሰልጣኝ ውበቱ በ2013 ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑን…

ባህር ዳር ከተማ ደግአረገ ይግዛውን በአሰልጣኝነት ሾመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደግአረገ ይግዛው የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ፡፡ የቀድሞው የክለብ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም አሠልጣኙ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖራቸውም ከቡድኑ ጋር እንደማይቀጥሉ መገለፁ ይታወቃል። ክለቡ በእርሳቸው…

የቻን ውድድር የምድብ ድልድል መስከረም 21 ቀን ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን (ቻን) ውድድር መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ ይሆናል፡፡ በ2023 በአልጄሪ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊዎችን ቁጥር ያደገ ሲሆን በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል፡፡…

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾመዋል። አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነዋል። ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንስትራክተርነት ፣ በአፍሪካ…

ፋሲል ከነማ ቡማሙሩን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪከ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ከቡሩንዲው ክለብ ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ 3 ለ ዐ አሸንፏል። በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አለም ብርሃን ይግዛው፣ፈቃዱ አለሙ እና ታፈሰ ሰለሞን የማሸነፊያ ጎሎችን አስቆጥረዋል። የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 6 ቀን የሚደረግ ይሆናል።

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።   

በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሐ ግብር ላይ አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች እንዳስመዘገቡት ውጤት ከአምስት ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር የሚደርስ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኢትዮ - ኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችውና በ18ኛው የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘችው ጎቲቶም ገብረስላሴ ልዩ ተሸላሚ…