Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በ1500 ሜትር በማንሃተን ከተማ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በኒዮርክ ማንሃተን በተካሄደው የሴቶች የ1500 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በውድድሩ አክሱማዊት አምባየ 1ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 2ኛ እና ፍሬወይኒ ሃይሉ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡ በፈረንጆች 2022 እየተካሄደ ያለው ይህ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ዛሬም ሌሎች ውድድሮችን በማካሄድ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…
Read More...

ሴኔጋል እና ሞሮኮ በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ጥር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሴኔጋል እና ሞሮኮ በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ተጋጣሚወቻቸውን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡ ምሽት አንድ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ሴኔጋል ኬፕ ቬርዴን 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለችው፡፡ ሴኔጋል ብልጫ በወሰደችበት ይህ ጨዋታ የማሸነፊያ ጎሎችን ሳዲዮ ማኔ እና ባምባ ዲዬንግ ከእረፍት መልስ…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዕቅዱን ማሳካት ባለመቻሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች የተቻላቸውን ጥረት ቢያደርጉም፤ ተይዞ የነበረውን እቅድ ማሳካት ባለመቻላቸው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ በድን በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ የነበረውን…

ቡበከር ናስር ለሙከራ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናቱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና የምንጊዜውም ኮከብ ግብ አግቢ አቡበከር ናስር ለሙከራ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቷል። አቡበከር ናስር ወደደቡብ አፍሪካ ያቀናው፥ የአገሪቱ ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውስ በጥር የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን ለማስፈረም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የዝውውር ድርድር ካደረገ በኋላ ነው፡፡…

ጋምቢያ በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጋምቢያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጋምቢያ ከጊኒ ጋር ባደረገችዉ ጨዋታ በሙሳ ባሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ሩብ ፍፃሜ መቀላቀል የቻለችዉ፡፡…

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻዉ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ጥር 15፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻዉ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ዛንዚባር ላይ በተደረገው ይህ ጨዋታ የታንዛኒያን የማሸነፊያ ጎል ክሪሲያ ጆንባራ በ64ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥራለች፡፡ መረጃዉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው ፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ራስ ሐይሉ ጅምናዚየም ዛሬ ተጀምሯል። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች…