ስፓርት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በካፍ የውድድር ፈቃድ አገኘ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በካፍ የውድድር ፈቃድ አግኝቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ በ2021-22 በሚዘጋጀው የአፍሪካ የሴቶች የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን ክለብ ከካፍ የውድድር ፈቃድ አግኝቷል።
ክለቡ በፋይናንስ ፣ ስፖርታዊ መስፈርት ፣ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይልና አስተዳዳር እንዲሁም የክለብ ህጋዊነትን የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ ካፍ በፈረንጆቹ ሐምሌ 2…
Read More...
በምሽቱ ዳይመንድ ሊግ ዮሚፍ ቀጀልቻ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ድል ቀንቶታል፡፡
ዮሚፍ በ3 ሺህ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሲሆን፥ ርቀቱን 7 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ ማጠናቀቁን የአፍሪካ ዩናይትድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ፋንቱ ወርቁ…
በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጃፓን ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጅት መደረጉን ተገለፀ።
ዝግጅቱን በማስመልከት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በሂልተን ሆቴን በጋራ መግለጫ ተሰጥተዋል።
የቶኪዮ…
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኑኖ ኢስፒሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ፖርቹጋላዊውን ኑኖ ኢስፒሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ፡፡
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በወልቭስ አራት አመታትን አሳልፈው በውድድሩ አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል፡፡
አሰልጣኙ ኤቨርተንን አልያም ክሪስታል ፓላስን ይይዛሉ ተብሎ ቢጠበቅም መዳረሻቸው ሰሜን ለንደን…
በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ እና ዩክሬን ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች እንግሊዝ እና ዩክሬን ድል ቀንቷቸዋል፡፡
እንግሊዝ ከጀርመን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች፡፡
የማሸነፊያ ግቦችን ራሂም ስተርሊንግ እና ሃሪ ኬን አስቆጥረዋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ዩክሬን…
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ::
ድጋፉ ኮሚቴው በጃፓን ቶኪዮ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለሚያደርገው ዝግጅት የሚረዳ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ድጋፉን ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር…
የሴካፋ ውድድር በሁለት ሳምንት ተራዘመ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ውድድር (ሴካፋ) በሁለት ሳምንት መራዘሙን አስታወቀ፡፡
ውድድሩ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀምር መገለጹን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፌዴሬሽኑ ውሳኔው የሴካፋ መሆኑን ገልፆ ከውድድሩ መጀመር ሶስት ቀናት በፊት ቡድኖች…