Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ጣሊያን የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በተካሄደው የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ጣሊያን እንግሊዝን በፍጽም ቅጣት ምት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን የሆነችው፡፡ ጨዋታው በተጀመረ 2ኛው ደቂቃ ላይ ሉክ ሻው እንግሊዝን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ 67ኛው ደቂቃ ላይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጣልያንን አቻ የሚያደርጋትን ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡…
Read More...

በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝና ጣሊያን ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ማምሻ በተደረገ ጨዋታ እንግሊዝ ዴንማርክን በማሸነፍ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ማለፏን አረጋገጠች፡፡ ጨዋታው በመደበኛ ሰዓት በአንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን በተጨመረ 30 ደቂቃ እንግሊዝ አንድ ጎል በማከል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ በዚህም ለአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ መድረሷን ያረጋጋጠች…

የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ስታዲየምን እድሳት ለማድረግ ከሁለት ሳምንት በፊት የውል ስምምነት መደረጉ ይታወሳል። በውሉ መሠረትም የእድሳት ስራው ዛሬ ተጀምሯል። ዕድሳቱ በቅድሚያ ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶች መሠረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን፥ የመጫወቻ…

በአውሮፓ ዋንጫ ጣሊያን ለፍጻሜ ደረሰች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ጣሊያንን እና ከስፔን ባገናኘው ጨዋታ ጣሊያን ድል ቀንቷታል፡፡ ጨዋታው በመደበኛ ሰዓት በአንድ አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ጣሊያን በመለያ ምት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ በዚህም ለአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ መድረሷን ያረጋጋጠች ሲሆን፤ ለፍጻሜው ጨዋታ ዛሬ ምሽት ከሚጫወቱት…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶችን ዝግጅት በልምምድ ስፍራ ተገኝተው ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን ወክለው በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚወዳደሩ አትሌቶችን ስልጠና እና ዝግጅት በልምምድ ቦታ ላይ ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የበላይ ጠባቂ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተገኝተው የተወዳዳሪዎችን ዝግጅት ከተመለከቱ በኋላ በማበረታታት መልካም ዕድል…

በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከ3 በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ማስፈረም እንደማይቻል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ  እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ዝውውርን የተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም ፌዴሬሽኑ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን በየትኛውም የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ከ3 በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማስፈረም እንደማይቻል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው የውጭ ሀገር ተጫዋቾች የዝውውር መመሪያ…

በፈረንሳይ በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አስመዘገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በፈረንሳይ በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አበረታች  ውጤቶችን አስመዝግበዋል። በዚህም በፈረንሳይ፣ ሌንስ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ያሲን ሃጂ  በ13 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጥላሁን ኃይሌ በ13 ደቂቃ 32 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን…