ስፓርት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቋም መለኪያ ጨዋታ ከኡጋንዳ አቻው ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን 1 ለ 0 አሽንፏል፡፡
የብሄራዊ ቡድኑን የአሸናፊነት ጎል የፋሲል ከነማው የመሐል ተጫዋች በዛብህ መለዮ 93ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጣይ እሁድ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ቀድም ሲል በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮንሺፕ /ቻን/ ውድድር ደቡብ ሱዳንን ያሸነፈ ሲሆን ከሩዋንዳ…
Read More...
ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራርነት የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫ አስፈፃሚው ኮሚቴ ከታዩ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንት እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡
በዚህም መሰረት 32 የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባለት ለመጨረሻ እጩነት ሲቀርቡ÷ 3 እጨዎች ደግሞ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት የመጨረሻ እጩዎች በመሆን ቀርበዋል፡፡
ይህ…
የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች የማጣሪያ ውድድር ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ውድድር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ተደልድላለች።
ኢትዮጵያ ይህን ዙር የምታልፍ ከሆነ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ አልጄሪያን የምትገጥም መሆኑን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው…
አቡበከር ናሰር ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጠረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናሰር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡
በአሬና ስታዲየም በተደረገው የሰንዳውንስ እና የካይዘር ቺፍስ ጨዋታ አቡበከር በ76ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በመግባት ነው ለክለቡ 4ኛውን ለራሱ ደግሞ የመጀመሪያውን ግብ ማስቆጠር የቻለው፡፡
…
ለአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር በስካይላይት ሆቴል ተካሄደ፡፡
በሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት…
በሻምፒዮናው 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የልዑካን ቡድኑ፥ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል…
በሻምፒዮናው 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገባ፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የልዑካን ቡድኑ÷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡…